Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትጅብ ጥላ ይጥላል? ያፈዛል?

ጅብ ጥላ ይጥላል? ያፈዛል?

ቀን:

በአገራችን በብዙ ቦታ ስለጅብ ሲነገር ‹‹ጅብ ጥላውን ከጣለ ሰው እንዳይንቀሳቀስ ያደርጋል፤ ያፈዛልም፤›› ተብሎ ይታናል፡፡ ይህ ግን ትክክለኛ አመለካከት አይደለም፡፡ እንዲህ ተብሎ እንዲታመን ያደረጉ ምክንያቶች ግን ይኖራሉ፡፡ አንደኛው ምክንያት በጉዞ ላይ ካሉ ሰዎች መካከል ደከም ያለና ወደ ኋላ የቀረው በጅብ ስለሚወሰድ ሲሆን፣ ሌላኛው በፍርሀት ምክንያት ከጅብ ጋር መፋጠጥ ድርቅ ብሎ መቅረትን ማምጣቱ ነው፡፡ እንዲህ ባይሆንማ በገጠር ከብቶች የሚመገቡት ቀርቦላቸው ሌሊቱን በቤት አቅራቢያ ውጪ እንዲያድሩ ሲደረጉ፣ ተንኮስ እያደረገ እንዲሮጡለትና እንዲያጠቃቸው ሙከራ ማድረጉን ትቶ በቀጥታ ባጠቃቸው ነበር፡፡ በሐረርና አካባቢው ያሉ ጅቦችንም በተመለከተ የውሻ ያህል ከሰው ጋር ቀርበው ሥጋ ሲጣልላቸው የሚበሉና ሥጋም እንዲጣልላቸው በሚመገቡ ሰዎች አካባቢ ያለምንም መተናኮል የሚንጐራደዱ ባልሆኑም ነበር፡፡      

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊጠቀስ የሚገባው ነገር በ1879ዎቹ በአገራችን የተከሰተው ክፉ ቀን የሚባለው ድርቅ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ጅቦች በየምሽቱ ያለምንም ከልካይ ወደየቤቱ እየገቡ በረሃብ የደከሙ ሰዎችን ይወስዱ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ በአዲስ አበባ ውስጥ ስለሆነው ነገር የዘገቡት አለቃ ለማ (የችጋርና ወረርሽኝ ታሪክ በኢትዮጵያ በሚለው መጽሐፍ ውስጥ) ‹‹በዚያን ጊዜ በጅቦች ከቤታቸው ሲወሰዱ፣ ወሰደን! ወሰደን! የሚል ጩኸት የሚያሰሙ ሰዎችን በየማታው አምስት ወይም ስድስት ጊዜ እየሰሙ መንቃት ግድ ነበር፤›› ብለዋል፡፡

በተቃራኒው ሰዎች ራሳቸውን ለመከላከል አቅም በሚያጡበት የከፋ የድርቅ ወቅት አውሬዎች የበላይነት ሊይዙ ቢችሉም፣ ሰዎችም በዚያው የመኖር ትግል ውስጥ ከሃይማኖትና ባህላቸው ውጪ በሆነ መልኩ የተለያዩ በደጉ ጊዜ የማይበሏቸውን እንስሳት ሲመገቡ መታየታቸው ተዘግቧል፤ ጅቦችንም ጨምሮ፡፡ በዚያም ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ‹‹ጅቡ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ›› የሚለው አባባል የመጣው፡፡

  • ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)

  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...