Thursday, December 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኢትዮጵያ መንግሥትና ተቋማትን በመሰለል የተጠረጠሩ ክስ ተመሠረተባቸው

የኢትዮጵያ መንግሥትና ተቋማትን በመሰለል የተጠረጠሩ ክስ ተመሠረተባቸው

ቀን:

በኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን በመመልመል መንግሥትንና ተቋማቱን እንዲሰልሉ፣ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን) ወይም ዴሞክራሲያዊ ምንቅስቃስ ሕዝቢ ትግራይ (ዴምሕት) ብሎ በሚጠራው ቡድን የተመለመሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

የወንጀል ድርጊት በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የአይዲዎሎጂ ዓላማን ለማራመድ፣ ሕዝብን ለማስፈራራትና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ የተመሠረተባቸው፣ ነዋሪነታቸው በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በሆኑት አቶ አማረ ተወልደና አቶ ታሪኩ በላይ ላይ ነው፡፡

ተከሳሾቹ የሽብር ቡድን ነው ከተባለው ድርጅት ጋር በስልክ በመገናኘት፣ አባል በመሆንና መመርያ በመቀበል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን በመመልመል፣ የኢትዮጵያ ተቋማትን በመሰለልና መረጃ አሳልፈው በመስጠት በሽብር ወንጀል ውስጥ የተሳተፉ መሆናቸውን፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተው ክስ ያስረዳል፡፡

አቶ አማረ ተወልደ የተባሉት አንደኛ ተከሳሽ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እያሉ ያውቋቸው የነበሩትንና አሁን ኤርትራ ከሚገኙት የትሕዴን ወይም ዴምሕት አመራር አቶ ጐይቶም በርሔ ጋር በተንቀሳቃሽ ስልክ እየተደዋወሉ (ስልክ ቁጥሩ ተጠቅሷል)፣ የግለሰቦችን ተንቀሳቃሽ ስልክ ይሰጡ እንደነበር፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ኢሕአዴግና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ እንዳይጠሩ እንደሚፈልግ፣ ሕዝቡ በስብሰባ እንዳይሳተፍ አፈና እንደሚያደርግና ሌሎች መረጃዎችን ይቀባበሉ እንደነበር ክሱ ያስረዳል፡፡

መንግሥት ያላደረገውን ነገር ግን በጭላ፣ በኢሮብና በማይጨው በሚገኙ የዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነት ፓርቲ አባላት ላይ ችግር እያደረሰባቸው መሆኑን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዓረና ፓርቲ ውቅሮ ከተማ ውስጥ የተሳካ ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረጉን፣ አቶ ብርሃነና አቶ አብርሃ በተባሉ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ስብሰባው መመራቱንና ዝርዝር መረጃ ይቀባበሉ እንደነበረ ክሱ ይዘረዝራል፡፡ መንግሥት ያላደረገውን እንዳደረገና በሕዝብ ላይ በደል የደረሰ በማስመሰል ሐሰተኛ መረጃ ሲያስተላልፍ እንደነበርም ይጠቁማል፡፡

በትግራይ ክልል የተለየ በደል በሕዝቡ ላይ እየደረሰ መሆኑንና ሌሎች መረጃዎችን ማስተላለፉንና በወልቃይት የስኳር ፋብሪካ ለመገንባት የአካባቢው ነዋሪዎች ያለምንም ካሳ እየተፈናቀሉ መሆኑን የሐሰት መረጃዎችን በማቀበል አገርን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ሁለቱም ተከሳሾች ትሕዴን/ዴምሕት የሚባል ስያሜ ያለው የሽብር ቡድን ውስጥ አባል በመሆንና ከቡድኑ አመራሮች ጋር በስልክ መረጃ በማስተላለፍ፣ በፈጸሙት በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ መሳተፍ ወንጀል እንደተከሰሱ ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሷል፡፡

ፓርላማው በሰኔ ወር 2003 ዓ.ም. በሽብርተኝነት የፈረጃቸው አምስት ድርጅቶች ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ አልቃይዳና አልሸባብ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በሽብርተኝነት ወንጀል ለመክሰስ ቢቻልም፣ አንድን ድርጅት ሽብርተኛ ለማለት የሚቻለው ፓርላማ ሲወስን ነው፡፡ ትሕዴን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀ ቡድን አይደለም፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...