አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 3 መካከለኛ ቲማቲም
- 2 የቡና ስኒ (200 ግራም) ሩዝ
- 1 መካከለኛ የታሸገ የቆርቆሮ አተር
- 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 3 የሾርባ ማንኪያ ቪኒገር ሶስ
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
አዘገጃጀት
- የሩዙን ሁለት እጥፍ የሚሆን ውኃ አዘጋጅቶ ጨው ጨምሮ መጣድ፤
- ውኃው ሲፈላ ሩዙን መጨመር፤
- ውኃውን ሲመጥ መብሰሉን አረጋግጦ ማውጣት፤
- ቲማቲሙን ለሁለት ከፍሎና ፍሬውን አውጥቶ ወፈር አድርጐ መክተፍ፤
- የታሸገውን የቆርቆሮ አተር ውኃውን ብቻ አስወግዶ አተሩን፣ ሩዙንና ቲማቲሙን መቀላቀል፤
- ቪኒገር ሶሱን ከላይ ካፈሰሱ በኋላ ቁንዶ በርበሬ ደባልቆ ማቅረብ፡፡
ደብረወርቅ አባተ፣ የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት፣ 1993 ዓ.ም.