በቀድሞው መሪ በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ሰብእናና ሕይወት ዙርያ ጭብጡን ያደረገ አዲስ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
በደራሲ ሀብታሙ አለባቸው ተጽፎ በሊትማን ቡክስ የታተመው መጽሐፍ፣ ‹‹የቄሳር እንባ›› የሚል ርእስ ያለው ሲሆን፣ የቀድሞውን መሪ ፖለቲካዊ ሥነልቦና፣ ቁመና እንዲሁም ፖለቲካዊ እሳቤያቸውን ይተነትናል፡፡
በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሆነው ያገለገሉት ደራሲው፣ ፖለቲካዊ ልቦለዶችን በመጻፍ ረገድ ይህ ሁለተኛው ሥራቸው ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በኢትዮ-ኤርትራውያን ፖለቲካዊ ሥነ ልቦና ዙርያ የጻፉት ‹‹አውሮራ›› ተጠቃሽ ነው፡፡
408 ገጾች ያለው ‹‹የቄሳር እንባ›› ሊትማን ቡክስ በ79 ብር ያከፋፍለዋል፡፡