ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በየካቲት 2008 ዓ.ም. ለሚያካሂደው የሥነ ሕዝብና የጤና ዳሰሳ ጥናት ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚያስችል ስምምነት መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) ጋር ተፈራረመ፡፡
ጥናቱ፣ ከፕሬዚዳንቱ አስቸኳይ የኤድስ ዕርዳታ ዕቅድ (ፔፕፋር) በተገኘ ከፊል ድጋፍ፣ በሥነ ተዋልዶና በቤተሰብ ዕቅድ ዝንባሌ፣ የሕፃናት የአመጋገብ ሁኔታ፣ ለሕፃናትና ለእናቶች በሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች፣ በቤተሰብ ዕቅድ፣ በኤችአይቪ ኤድስ ዙሪያ ያለ ግንዛቤና የበሽታው የሥርጭት ሁኔታ ላይ ወቅታዊና ተአማኒነት ያለው መረጃ በማቅረብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የሥነ ሕዝብና ጠና ዳሰሳ ጥና ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚያስችለውን ስምምነት የተፈራረሙት፣ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዴኒስ ዌለር ናቸው፡፡