Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየወጣቶች የተዘዋዋሪ ፈንድ መመርያ ወጣለት

የወጣቶች የተዘዋዋሪ ፈንድ መመርያ ወጣለት

ቀን:

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ለወጣቶች በተዘዋዋሪ ፈንድ ብድር ለመስጠት የሚያስችለውን መመርያ አወጣ፡፡

በመመርያው መሠረት የተደራጁ ወጣቶች እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይኼም ብድር ከአምስትና ከዚያ በላይ ለሚደራጁ ወጣቶች ይሰጣል፡፡

መንግሥት ለበጀት ዓመቱ አሥር ቢሊዮን ብር ያዘጋጀ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ ግማሹ በስድስት ወራት ውስጥ ለወጣቶች ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለወጣቶች የሥራ ፈጠራ የሚውለው ብድር በስምንት በመቶ ወለድ ለወጣቶቹ ይሰጣል፡፡ ሁለት በመቶው የሚሆነው የንግድ ባንክ ድርሻ ሲሆን፣ ቀሪው ስድስት በመቶ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ይሆናል፡፡

ብድሩን የሚያገኙት ወጣቶች በሚሰማሩበት የሥራ ፈጠራ መስክ የውጤታማነት ጊዜና የሥራው ባህርይ መሠረት፣ ብድሩን ከአንድ እስከ አምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከፍለው እንዲጨርሱ ይጠበቃል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ብድሩን የሚያገኙት ወጣቶች የተበደሩትን አሥር በመቶ እንዲቆጥቡ ይደረጋል፡፡

ይኼ የተዘዋዋሪ ፈንድ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) በተያዘው የበጀት ዓመት የሁለቱን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር የተገለጸ ሲሆን፣ በወቅቱም ይኼ ፈንድ ለሥራ ፈጠራ እንደሚውል ተናግረው ነበር፡፡

በወቅቱም በአማራና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልሎች ውስጥ ተከስቶ ለነበረው ብጥብጥና ሁከት ሥራ አጥነት እንደ ምክንያት በመንግሥት ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡ ይኼ ፖለቲካዊ ይዘት የነበረው ሁከት የመቶዎችን ሕይወት ቀጥፎ አልፏል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ወጣቶችን በሚመለከት ስትራቴጂና ፓኬጅ እንደወጣ ይታወሳል፡፡ እንዲሁም በቅርቡ የተወካዮች ምክር ቤት የአሥር ቢሊዮን ብር ብድር ለማቅረብ የሚያስችለውን አዋጅ አፅድቋል፡፡

በወጡት ስትራቴጂና ፓኬጅ መሠረት መንግሥት የወጣቶችን ችግር ለመፍታት የተለያዩ የሥራ ፈጠራዎችን እንደሚተገብር መግለጹ ይታወሳል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ወጣቶቹን በትልልቅ ፕሮጀክቶች እንዲሳተፉ ማድረግ፣ በገጠር ውስጥ ያለውን የእርሻ መሬት እጥረት ባገናዘበ ሁኔታ መሬት መስጠትና መልሶ የማስፈር ፕሮግራሞች ይገኙበታል፡፡

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአሁኑ ጊዜ ከአገሪቷ አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ወደ 71 በመቶ የሚጠጋው ከሰላሳ ዕድሜ በታች ይገኛል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ 22 በመቶ የሚሆነው ዕድሜው ከ15 እስከ 29 ያለው ወጣት ሥራ አጥ ነው፡፡ የአገሪቱ አጠቃላይ የሥራ አጥ መጠን 22 በመቶ ደርሷል፡፡ ከዚህም ውስጥ በከተማዎች የሥራ አጥ ቁጥሩ 17 በመቶ እንደደረሰ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ንግድ ባንክ በተሰጠው ፈንዱን የማስተዳደር ሥልጣን መሠረት ጥያቄዎችን ከማይክሮ ፋይናንሶች እየተቀበለ ያስተናግዳል፡፡

‹‹እስካሁን ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የደረሰን ጥያቄ የለም፤›› ሲሉ የባንኩ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰ፣ ‹‹እስካሁን ወጣቶቹን የመመልመልና የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፤›› ሲሉ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

‹‹ጥያቄዎቹ ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እንደደረሱን ገንዘቡን ለመልቀቅ ዝግጁ ነን፤›› ሲሉም ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የባንኩ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...