Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዶ/ር ደብረ ጽዮን በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦታ በአደዋ ይወዳደራሉ

ዶ/ር ደብረ ጽዮን በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦታ በአደዋ ይወዳደራሉ

ቀን:

ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ በተካሄዱት አራት ጠቅላላ ምርጫዎች የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተወዳደሩበት በአደዋ የምርጫ ክልል  ለመጀመሪያ ጊዜ በዘንድሮ ምርጫ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ኢሕአዴግን ወክለው እንደሚወዳደሩበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመጪው ግንቦት በሚካሄደው አምስተኛ ጠቅላላ ምርጫ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር የትውልድ ቦታና ጠንካራ የፖለቲካ ይዞታ ወክለው፣ ለተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩት የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት ዶ/ር ደብረ ጽዮን የሕወሓት ነባር ታጋይ ሲሆኑ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበርና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው በማገልገል ላይ ይግኛሉ፡፡

ዶ/ር ደብረ ጽዮን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲወዳደሩ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ወደ ፌዴራል መንግሥት ከመምጣታቸው በፊት በደቡብ ትግራይ ክልል ምክትል ዋና አስተዳዳሪ፣ በኋላም የትግራይ ክልል የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡

የአደዋ ከተማ ተወላጅ የሆኑት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ወደ ትጥቅ ትግል ከመግባታቸው በፊት፣ ከተማውን በመወከል ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋች እንደነበሩ የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡

አደዋን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአራት ተከታታይ ምርጫዎች የተወዳደሩት ሟቹ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሕወሓትን ከ1977 ዓ.ም. ጀምሮ ኢሕአዴግም ከተመሠረተበት ከ1981 ዓ.ም. ጀምሮ በሊቀመንበርነት የመሩ ሲሆን፣ መጀመሪያ ለሦስት ዓመታት የሽግግር መንግሥቱ ፕሬዚዳንት፣ ቀጥሎም እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገሪቱን መምራታቸው ይታወሳል፡፡

በአራተኛው ጠቅላላ ምርጫ የቀድሞዋ ሕወሓት ታጋይ ወ/ት አረጋሽ አዳነ ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት ፓርቲ አባል የሆነበትን መድረክ በመወከል፣ ከቀድሞ የትግል ጓዳቸው ከአቶ መለስ ጋር መፎካከራቸው አይዘነጋም፡፡ በአሁኑ ምርጫ ግን ዶ/ር ደብረ ጽዮንን የሚወዳደረውን ተፎካካሪ ዕጩ ማወቅ አልተቻለም፡፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዕጩ ተወዳዳሪዎችን የመጨረሻ ዝርዝር የያዘውን ቅጽ አራት በመባል የሚታወቀውን ሰነድ ይፋ ባለማድረጉ፣ በተለይ የኢሕአዴግና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚወዳደሩባቸውን የምርጫ ክልሎች ለማወቅ አልተቻለም፡፡ ባለፈው ሳምንት ዋነኛ የኢሕአዴግና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጩዎች በአዲስ አበባ የሚወዳደሩበትን ይፋ ያልሆነ ዝርዝር ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...