Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት አተትን መከላከል እንዳልቻለ ተገለጸ

የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት አተትን መከላከል እንዳልቻለ ተገለጸ

ቀን:

የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት አተትን መከላከል እንዳልቻለ የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ ይህ የተገለጸው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ጉባዔውን ከጥቅምት 28 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታት የአተት በሽታ በአገሪቱ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰም በጉባዔው ተጠቁሟል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩን ጨምሮ የክልል የጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ የሆስፒታል ዳይሬክተሮች፣ ሐኪሞች፣ የክልል የካቢኔ ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የጤና ጉባዔ የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ታሪኩ በላቸው የአተት በሽታ ለአገሪቱ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓቱ ደካማ በመሆኑ ምክንያት በተከታታይ ሦስት ዓመታት በሶማሌ፣ በትግራይና በአማራ ክልሎች በተከሰተው የአተት በሽታ የበርካታ ዜጎች ሕይወት እንዳለፈም መግለጻቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ ቢሆንም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ትኩረት ባለመስጠቱ ምክንያት፣ በየዓመቱ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ምክትል ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ኃላፊዎችም ችግሩ እንዳለ በማመን በቀላሉ ማስቆም የሚቻለውን በሽታ ተገቢው ሥራ ባለመከናወኑ ምክንያት በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ መግለጻቸው ታውቋል፡፡

የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት በተገቢው ሁኔታ ተግባራዊ ባለመሆኑ ምክንያት ችግሩ እንደተከሰተ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ መግለጹን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በጉባዔው ላይ በ2009 ዓ.ም. አገሪቱ እየተከተለችው ካለው የጤና ጥበቃ ፖሊሲ አንፃር ውጤታማ ሥራ የሠሩ ክልሎች መሸለማቸው ታውቋል፡፡ በሽልማቱ ከተካተቱ ክልሎች መካከል ትግራይና አማራ ክልሎች እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን፣ ተሸላሚ ያልነበረው የኦሮሚያ ክልል በመድረኩ ላይ ቅሬታ ማቅረቡም ታውቋል፡፡ በወቅቱም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ኃላፊዎችና በክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊዎች መካከል መለስተኛ ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ኦሮሚያ ክልል ከሌሎች ክልሎች ያነሰ አፈጻጸም እንዳላሳየ የክልሉ ተወካዮች መግለጻቸውም ተጠቁሟል፡፡

በጉባዔው ላይ ለብዙ ዓመታት ደም በመለገስ የሚታወቁ ግለሰቦችና በጤናው ዘርፍ የተሻለ ሥራ ያከናወኑ ባለሙያዎች ሽልማት እንዳገኙ ታውቋል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት የአገሪቱ የጤና ጉባዔም በመቐለ ከተማ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...