Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊባለፉት ሰባት ወራት በፌዴራል ዳኞች ላይ ከ60 በላይ አቤቱታዎች ቀረቡ

ባለፉት ሰባት ወራት በፌዴራል ዳኞች ላይ ከ60 በላይ አቤቱታዎች ቀረቡ

ቀን:

በተያዘው በጀት ዓመት ያለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ከ60 በላይ የዲሲፕሊን አቤቱታዎች በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሚሠሩ ዳኞች ላይ ቀረቡ፡፡

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ መድኅን ኪሮስ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሰባት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት፡፡

ዳኞች የሚፈጽሟቸውን የዲስፕሊን ጥሰቶችን በተመለከተ ማንኛውም ኅብረተሰብ አቤቱታውን ለዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ማቅረብ እንደሚችል በሕግ ተደንግጓል፡፡ በዚህ መሠረት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ለዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽሕፈት ቤት 50 የዲሲፕሊን አቤቱታዎች መቅረባቸውን፣ አቤቱታዎቹ በፍርድ ምርመራ ባለሙያዎች አማካኝነት በመጣራት ላይ መሆናቸውን ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች 19 አቤቱታዎች ለዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ቀርበው 15 ያህሉ በዲስፕሊን የማያስጠይቁ በመሆናቸው ውድቅ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተቀሩት አምስት ዳኞችን የሚመለከቱ አራት አቤቱታዎች የሚያስጠይቁ በመሆናቸው ሦስቱ ዳኞች በጽሑፍ ምላሽ እንዲሰጡ መወሰኑን ጠቁመዋል፡፡ ከተቀሩት ሁለት ዳኞች መካከል አንዱ ጉባዔው ፊት ቀርበው የቀረበባቸውን ውሳኔ እንዲያስተባብሉ፣ አንደኛው ዳኛ ደግሞ ከሥራቸው ታግደው ለጉባዔው በጽሑፍ መልስ እንዲሰጡና በአካል ቀርበውም እንዲያስረዱ ተወስኖ ተግባራዊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሠረት ተጠያቂ ከሆኑት አምስት ዳኞች መካከል አንድ ዳኛ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ አንድ ሌላ ዳኛ ደግሞ የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በተጨማሪም አንድ ዳኛ የቀረበባቸውን አቤቱታ በአግባቡ በማስተባበላቸው ነፃ እንዲሆኑ፣ ሌላው ዳኛ ደግሞ ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸውንና ጉባዔው የሚወስደውን ዕርምጃ ለመወሰን ተጨማሪ ማስረጃዎችን በማየት ላይ እንደሚገኝ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ለፓርላማው አስረድተዋል፡፡

ከዚህ የዲስፕሊን አቤቱታ ውጪ ደግሞ በሙስና ወንጀል ሁለት ዳኞች ተከሰው ጥፋተኛ መባላቸውን ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ መድኅን ሪፖርት አድርገዋል፡፡

በወንጀል ጥፋተኛ የሆኑ ዳኞች ከዳኝነት ሥራቸው እንዲነሱ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79(4)(ሀ) የሚያዝ በመሆኑ፣ በዚሁ አግባብ አስተዳደር ጉባዔው ወስኖ የሾማቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሹመቱን እንዲያነሳ መተላለፉን ገልጸዋል፡፡ በእስካሁኑ ሒደት ግን ፓርላማው በዚህ በጀት ዓመት ከሹመት ያነሳው ዳኛ አለመኖሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ‹‹የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን ማሳደግ›› በሚል ንዑስ ርዕስ ባቀረቡት ሪፖርት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለመለካት የተቀመጡ መሥፈርቶች በአግባቡ መተግበራቸውን መከታተልና መገምገም መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የዳኝነት ጥራትን በተመለከተ ሪፖርቱ በተዘጋጀበት ወቅት ከጥራት መመዘኛ ነጥቦች አኳያ ከተገልጋዮች መሰባሰብ የሚገባቸውን መረጃዎች ማግኘት ባይቻልም፣ የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን ከዳኞች ወርኃዊ የአፈጻጸም ግምገማ ሪፖርቶች መረዳት መቻሉን ይገልጻል፡፡

በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ነፃነትና ገለልተኝነት ዙሪያ እንቅፋት የሚፈጥሩ አመለካከቶችን፣ አሠራሮችን፣ አደረጃጀቶችን ወይም አቅርቦቶቹን ለይቶ ማስተካከያዎችን ለማመላከት የችሎቶችና የመዛግብት ቁጥጥር ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን፣ የችሎቶች ወርኃዊ አፈጻጸም ሪፖርቶችን በመገምገም ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞችን እንዲሁም በቀጣይነት መስተካከል የሚገባቸው የለውጥ አመለካከት ክፍተቶችን መለየት እንደተቻለ ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ በሪፖርታቸው መጨረሻ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎችን የጠቀሱ ቢሆንም፣ የዳኝነት ዲሲፕሊን ጉዳይ ግን እንደ ችግር በሪፖርቱ ማጠቃለያ ላይ አልተጠቀሰም፡፡

አጋጠሙ ከተባሉት ችግሮች መካከል አንዱ ከፍርድ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ የመሬት አስተዳደር ለሚቀርብለት የአፈጻጸም ጥያቄ የተሟላ መረጃ አለመስጠት፣ ባለድርሻ አካላት ፍርድ ቤትን አክብረው ወቅታዊ ምላሽ አለመስጠት፣ በፍርድ አፈጻጸም ሒደት ፖሊስና የቀበሌ መስተዳደር ተገቢውን እገዛና ትብብር አለማድረግ፣ የአፈጻጸም ውሳኔ የተሰጠበትን ንብረት የፍርድ ባለዕዳዎች ማሸሽ ይገኝበታል፡፡ ችግሩን ለመፍታት የተወሰዱ የመፍትሔ ዕርምጃዎች የፍርድ ቤት ውሳኔዎች ግልጽና የማያሻሙ ሆነው እንዲቀርቡ፣ ከዳኞችና ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ለመፍታት ጥረት መደረጉን ይገልጻል፡፡ 

የፓርላማው የሕግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተለይ የዳኞች ዲሲፕሊንን በተመለከተ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባና የዳኞች ምልመላ ላይም ተገቢው ትኩረት እንዲስጥ አሳስቧል፡፡        

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...