Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር በፀጥታ ችግሮች ሳቢያ መቀነሱ አሳስቦኛል አለ

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር በፀጥታ ችግሮች ሳቢያ መቀነሱ አሳስቦኛል አለ

ቀን:

  • በዩኒቨርሲቲዎች የተቋረጠው የታሪክ ትምህርት በሁለተኛ ደረጃ ምህርት ቤቶች እንዲሰጥ ተወሰነ

ከመስከረም ወር ጀምሮ በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት የሚጠበቅባቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር መቀነሱ እንዳሳሰበው፣ ትምህርት ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ታዬ (ዶ/ር) 2010 ዓ.ም. የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለምክር ቤቱ የከፍተኛ ትምህርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰኞ ኅዳር 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ሲያቀርቡ እንደተናገሩት፣ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የተመደቡና ነባር ተማሪዎች ከመስከረም ወር ጀምሮ በትምህርት ተቋሞቹ ተገኝተው መመዝገብና ትምህርት መጀመር የሚጠበቅባቸው ቢሆኑም፣ በርካታ ተማሪዎች እስካሁን በትምህርት ገበታ ላይ አልተገኙም፡፡

 በተለየ ሁኔታ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚታየው አለመረጋጋትና የፀጥታ ችግር ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዳይገኙ ምክንያት እንደሆነም ገልጸዋል። ተመዝግበው ትምህርት የጀመሩ ተማሪዎችም አቋርጠው መውጣት መጀመራቸውን ጠቁመው፣ ይህም አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነባቸው ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

- Advertisement -

 ችግሩን በተመለከተ ከሚመለከታቸው የክልል አመራሮች ጋር በመነጋገር መፍትሔ የሚሰጥ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን ተናግረዋል። ሰሞኑን ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር ቆይታ ያደረጉት የፓርላማው አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ አሳስበዋል። ‹‹ትምህርት ማቋረጥ የትግል ሥልት አይሆንም፡፡ ያልተማረ ሕዝብ ለኦሮሞ ሕዝብ ሊጠቅም አይችልም፤›› ብለዋል።

በመቱ ዩኒቨርሲቲ ሰሞኑን በተቀሰቀሰ ግጭት ትምህርት መስተጓጎሉን መረጃዎች ያመለክታሉ። በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ማቋረጥ ምክንያቱ ከፀጥታ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ የአዋሽ ወንዝ መሙላት በርካታ ነዋሪዎችን ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ያፈናቀለ በመሆኑ፣ የመጀመሪያናሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ቁጥር በኦሮሚያ ከፍ እንዲል እንዳደረገው ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትምህርት ሚኒስቴር ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረበው ሪፖርት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ ትምህርት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 2011 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚሰጥ አስታውቋል። የትምህርት ሥርዓቱ ተቀርፆ የመጽሐፍ ኅትመት እየተከናወነ እንደሚገኝ የገለጹት የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች፣ መጪው ትውልድ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ታሪክ ጠንቅቆ እንዲያውቅ ታልሞ የተቀረፀ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የሚስተዋለው አለመረጋጋት ብሔር ተኮር ይዘት እንዳለውና ይህንንም ላለፋት ሁለት አሥርት ዓመታት አገሪቱ የመጣችበት መንገድ የወለደው እንደሆነ የታሪክ ምሁራን ይስማሙበታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ 2008 ዓ.ም. ከዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋር በወቅቱ በነበረው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ትኩሳቶችና የኢትዮጵያን አንድነት በማጠንከር ዙሪያ በመከሩበት ወቅት ጥያቄ ካነሱት ምሁራን መካከል፣ ታዋቂው የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ አንዱ ነበሩ። ፕሮፌሰር ባህሩ በወቅቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበውት በነበረው ጥያቄ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ ትምህርት በዩኒቨርሲቲዎች እንዳይሰጥ ተከልክሎ የኢትዮጵያ አንድነትን ማጠንከር እንደማይቻል ጠቅሰው፣ ይህ ትምህርት እንዲቋረጥ በመደረጉም ማስረጃ የሌላቸውእውነትነታቸው ያልተረጋገጡ ንግርቶች የአገሪቱን ሕዝቦች አብሮነት እያዛቡ እንደሆነና የወቅቱ ፖለቲካዊ ክስተቶችም የዚህ መገለጫ ለመሆን እንደሚችሉ በጥያቄ መልክ አንስተው ነበር።

 በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት ምላሽ ምሁራኑ አጥንተው የመፍትሔ ሐሳብ ቢያቀርቡላቸው እንደሚያጤኑት ገልጸው፣ ያለፈው ታሪክ መልካምም ሆነ በጎ የጋራ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ ስለመሆኑ ጠቁመው ነበር። የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ እንዲሰጥ መወሰኑ የዘገየ ነገር ግን ተገቢ ውሳኔ መሆኑን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የታሪክ ተመራማሪዎች ገልጸው፣ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እንዲቀጥል ሊደረግ ይገባል ሲሉም ይከራከራሉ።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...