Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየእግር ኳሱ ፖለቲካዊ ጡዘትና ዕጣ ፈንታው

የእግር ኳሱ ፖለቲካዊ ጡዘትና ዕጣ ፈንታው

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሥረኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 30 እና ኅዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አከናውኗል፡፡ ከስፖርታዊ ባህሪው ይልቅ ክልላዊ በሚመስል የፖለቲካ ጡዘት ለሁለት ቀን ትርጉም አልባ ውይይት አድርጎ መጠናቀቁ በተነገረለት በዚሁ ጉባዔ፣ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው የአስመራጭ ኮሚቴ ሳይሰየም መቅረቱ ሰሞነኛ ጉዳይ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡

ጉባዔው ከመነሻው የፌዴሬሽኑን አዲስ ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ማካሄድ ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር፡፡ ይሁንና የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የምርጫውን ሒደትና ሥርዓት ከዚያው ከፌደሬሽኑ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ በላከው ማስጠንቀቂያ መሠረት ምርጫው ለ45 ቀናት እንዲራዘም ጉባዔው በአብላጫ ድምፅ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

የዚሁ ድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት በራሱ ከመነሻው አጀንዳ ተይዞለት በጉዳዩ ውይይት ተደርጎበት፣ ይኸው አጀንዳ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ መደገፍ ነበረበት የሚሉም አሉ፡፡ ይሁንና የጉባዔው ታዳሚዎች ወትሮም ቢሆን መሠረታዊ በሚባለው የእግር ኳሱ ክፍተት ላይ ከመምከር ይልቅ፣ በክልላዊ ስሜት ታጭቀው የመጡ በመሆናቸው ምክንያት የፌዴሬሽኑን መተዳደሪያ ደንብ ከቁብ ሳይቆጥሩት ምርጫው በእጅ ብልጫ ብቻ እንዲራዘም መደረጉ አይዘነጋም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የምርጫው መራዘም ከተወሰነ በኋላ የጉባዔው ትልቁ አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ‹‹የውኃ ሽታ›› ሆኖ የቀረው የአስመራጭ ኮሚቴ ጉዳይ እያነጋገረ ይገኛል፡፡ እንደ ሪፖርተር ምንጮች ከሆነ፣ ፌዴሬሽኑ ይህንኑ አካል ለመሰየም አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ ግፊት እየበዛበት ነው፡፡ ምክንያቱም ላለፉት አራት ዓመታት ተቋሙን ሲያስተዳድሩ ከነበሩት አመራሮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በድጋሚ ለምርጫው ዕጩ በመሆናቸው ከምርጫው መራዘም ጋር ተያይዞ አንዳንድ ክልሎች አዳዲስ ዕጩዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህም የተነሳ ወትሮም ቢሆን ‹‹በብልሹ የጋራ አመራር›› ምክንያት ወቀሳ ሲቀርብበት የነበረው ነባሩ አመራር፣ ከታኅሣሥ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፋር ለሚጠበቀው ምርጫ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የተላበሰ ሥራ ይሠራል ተብሎ እንደማይጠበቅ በመግለጽ ሥጋታቸን የሚገልጹም አሉ፡፡ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት የትግራይ ክልል የወከላቸው የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ ውክልና ከተነፈጋቸው ይጠቀሳሉ፡፡ በመሆኑም ምርጫው በተያዘለት ዕቅድ መሠረት መከናወን ይችል ዘንድ አሁን ያለው አመራር አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ ማድረግ የግድ መሆኑንም ይገልጻሉ፡፡

በተመሳሳይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለፕሬዚዳንታዊና ለሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ያቀረባቸው አቶ ጁነዲን ባሻና አቶ አበበ ገላጋይ ለምርጫው የመቅረባቸው ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ መግባቱ እየተነገረ ነው፡፡ ባለው ሁኔታ ቀደም ሲል በክልል ተወካይነታቸው በይፋ ሲነገርላቸው የቆዩ የሌሎች ክልሎች ዕጩዎችም ዕጣ ፈንታ ገና ያለየት መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...