አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 1 ኪሎ ግራም ቲላፒያ
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በደቃቁ የተከተፈ ቲማቲም
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የቲማቲም ድልህ
- 12 የሾርባ መንኪያ (200 ሚሊ ሊትር) ዘይት
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 መካከለኛ ሎሚ
- 2 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
አዘገጃጀት
- ዓሣውን ካፀዱ በኋላ አምስት ቦታ ከፍሎ በሥጋ መጠፍጠፊያ ጠፍጥፎ የሎሚውን ጭማቂ ላዩ ላይ አርከፍክፎ ማስቀመጥ፤
- ቀይ ሽንኩርቱን በዘይት ካቁላሉ በኋላ የቲማቲም ድልሁንና ነጭ ሽንኩርቱን መጨመር፤
- የተከተፈውን ቲማቲምን ጨምሮ ትንሽ ማማሰል፤
- ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ በደንብ ማብሰል፤
- ዓሣውን ጨምሮ በዝግታ እንዳይፈረካከስ እየተጠነቀቁ በማገላበጥ ማብሰል፤
- ከድንች ጥብስና ከስፒች ጋር አብሮ ሊቀርብ ይችላል፡፡
- ደብረወርቅ አባተ፣ የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት፣ 1993 ዓ.ም.