Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአምስት ዓመት የፍትሕ አፈጻጸም በአንድ ሳምንት ሊገመገም ነው

የአምስት ዓመት የፍትሕ አፈጻጸም በአንድ ሳምንት ሊገመገም ነው

ቀን:

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፍትሕ ሚኒስቴርና የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ከሚያዝያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሚያከብሩት የፍትሕ ሳምንት፣ የአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የፍትሕ አፈጻጸም እንደሚገመገም ተገለጸ፡፡

‹‹ፍትሕና ሁለንተናዊ ዕድገት›› በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የፍትሕ ሳምንት፣ በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የፍትሕ አፈጻጸም ምን ይመስል እንደነበር፣ ከኅብረተሰቡ አንፃር ምን ውጤት እንደተመዘገበና ያልተፈጸሙ ተግባራት ምን ምን እንደሆኑ ግምገማ እንደሚደረግባቸው፣ የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ልዑል ካህሳይ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው እንዳብራሩት፣ ለአምስተኛ ጊዜ የሚከበረው የፍትሕ ሳምንት ለሰላም፣ ለቀልጣፋና ፍትሐዊ ለሆነ ልማት መረጋገጥ፣ ሥር የሰደደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲገነባና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

ለበዓሉ መከበር ዋናው ምክንያት ከ2002 ዓ.ም. በኋላ አጠቃላይ የፍትሕ ሥርዓቱ የተሟላ የለውጥ ትግበራ የተጀመረበት ጊዜ መሆኑና የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ የአምስት ዓመት ፕሮግራምም እየተጠናቀቀ በመሆኑ፣ የበዓሉ ዋና ተዋናይ የሆኑት ተቋማት፣ ተቀናጅተው ሲሠሩ የከረሙትን አፈጻጸም የሚገመገምበትና ውጤቱና ድክመቱ የሚለይበት መሆኑን አቶ ልዑል ተናግረዋል፡፡

የለውጥ ሒደት የፍትሕ አካላቱ ለብቻቸው በተናጠል የሚያካሂዱት ሒደትና እንቅስቃሴ አለመሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን የሠራውንና አገልግሎቱንም ሕዝቡ እንዴት እያገኘ እንደሆነ ሐሳቡን የሚገልጽበት መድረክ መፍጠሪያም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ኅብረተሰቡ የራሱ ድርሻ ምን እንደሆነ ለይቶ የሚያውቅበትና የፍትሕ አካላቱን ከመደገፍ አንፃር የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለማስቻል በዓሉ ወሳኝ መሆኑንም አክለዋል፡፡ ከኅብረተሰቡ ግብዓትና ትችትም መቀበል ጠቃሚ በመሆኑ፣ በዓሉ አገራዊ ባህሪ ይዞ በፌዴራል ብቻ ሳይሆን በክልልም እንደሚካሄድ አቶ ልዑል አስታውቀዋል፡፡

በበዓሉ ላይ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱ፣ ኤግዚቢሽን መኖሩን፣ ጥሩና ምርጥ ተሞክሮዎች እንደሚቀርቡ፣ የእግር ጉዞ እንደሚደረግ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና በርካታ ሕዝብ የሚሳተፍበት የፍትሕ ሳምንት እንደሚሆንም ሚኒስትር ዴኤታው አመልክተዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...