Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበእንጥልጥል ላይ ያለው የማሪያኖ ባሬቶ አሠልጣኝነት

በእንጥልጥል ላይ ያለው የማሪያኖ ባሬቶ አሠልጣኝነት

ቀን:

ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተው የአሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶን ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ በአንክሮ የሚከታተሉ ወገኖችን በተለመደው ሁኔታ ያስገረመው ብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ለዓመታት ተጭነውት የቆዩ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ነቃሽ ማጣታቸው ነው፡፡ አንድ አሠልጣኝ ለመቀጠርም ሆነ ለማባረር የሚያበቁት ሕግን የተከተሉ መሥፈርቶች በግልጽ ተቀምጠው ሳለ በስሜታዊነትና በግዳጅ ተነሳስቶ ዕርምጃ መውሰድ በምንም መልኩ የማያዋጣ መሆኑን የሚገልጹ የስፖርቱ ቤተሰቦች አሁንም ሊመጣ የሚችለውን በመተንበይ ሥጋታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡

ሕዝቡ እንደ ውጤት ጥማቱ በአሠልጣኙም ላይ ሆነ በተጨዋቾች ላይ ቅሬታውን ሊገልጽ ይችላል፤ ይህም የተለመደና በየትም አገር የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ይሁንና የሕዝቡን ስሜት የማዳመጥና ጥያቄውንም በተገቢው መንገድ ለመመለስ ኃላፊነቱ የተጣለበት አካል ግን ከስሜታዊነት መገደብና ሕግን መሠረት ያደረገ አካሄድ ሊኖረው ይገባል ሲሉም አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ለዚህም ዋነኛው መፍትሔ የፌዴሬሽኑን አደረጃጀት በዘመናዊነት፣ በባለሙያ ተዋጽኦና ግልጽነትን በተላበሰ መልኩ መሆን እንዳለበትም ይመክራሉ፡፡

ለመነሻነት እንዲጠቅም ታስቦ የተወሰደው የአሠልጣኙ ጉዳይ የዚህ ጽሑፍ ትኩረት አይደለም፡፡ ይሁንና ‹‹የልብ አያደርስ›› እየተባለ ጠዋትና ማታ የስፖርት ቤተሰቡ መነጋገሪያ እየሆነ የሚገኘው የፌዴሬሽኑ አሠራር ጭምር የመፍትሔ አቅጣጫ ሊቀመጥለት ግድ እንደሚል እየተነገረ ይገኛል፡፡

ከ11 ወር በፊት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን እንዲያሠለጥኑ በይፋ የተቀጠሩት ፖርቱጋላዊው አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ዋሊያዎቹን ይዘው የወዳጅነት ጨዋታዎችን ጨምሮ ከ13 በላይ ጨዋታዎችን ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ይሁንና አሠልጣኙ በእነዚህ ሁሉ ጨዋታዎች የነበሯቸው ጠንካራና ደካማ ጎኖች ሳይገመገሙ ቆይተው ባሳለፍነው ሳምንት የፌዴሬሽኑ ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ፣ ማሪያኖ ለብሔራዊ ቡድኑ እንደማይመጥኑ፣ ከፌዴሬሽኑ በተለይም ከብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴውና ቴክኒክ ዲፓርትመንት ባለሙያዎች ጋር ተግባብተው ለመሥራት ፈቃደኛ ሳይሆኑ እንደቆዩና ንቀትም እንደነበረባቸው፣ ከሁሉም በላይ የአንድ አሠልጣኝን ቆይታ ከሚወስነው ውጤት አኳያም ቢሆን ሥራቸው ተስፋ ሰጭ እንዳልሆነ የሚገልጽ ሪፖርት ለፌዴሬሽኑ ማቅረቡ  ተሰምቷል፡፡ ይኼው ሪፖርት ባለፈው ዓርብ (መጋቢት 11 ቀን 2007 ዓ.ም.) ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ቀርቦ፣ ‹‹አንድ አሠልጣኝ ሊገመገምባቸው የሚገቡ መሠረታዊ ቴክኒኮችን ያሟላ የግምገማ ሪፖርት አይደለም፤›› በሚል ሪፖርቱን መሠረት ያደረገ ውሳኔ ሳያስተላልፍ፣ ይልቁንም አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ብሔራዊ ቡድኑን ማሠልጠን በጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ የነበሩባቸውን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን እንደገና ገምግሞ ለውሳኔ ሐሳብ የሚያቀርብ አዲስ ኮሚቴ እንዲቋቋም ስለመደረጉም ታውቋል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑን እያስተዳደረ የሚገኘው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአገልግሎት ጊዜውን ግማሽ ዘመን እያጠናቀቀ ይገኛል፡፡ የአሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶን የሥልጠና ብቃት እንዲገመግም ኃላፊነት የተጣለበት ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴም የኮሚቴው አንዳንድ አባላት እንደሚሉት ውጤትን መሠረት ያደረገ ግምገማ ተደርጎ ሪፖርቱ ውድቅ ቢደረግበትም፣ ግን ደግሞ የኮሚቴው የሙያ ብቃት ሳይታመንበት ይህን ያህል ጊዜ በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መቆየት እንዳልነበረበት ያምናሉ፡፡ ይኼው በተለይም የሰሞኑን በፌዴሬሽኑ የብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴው የደረሰበትን የግምገማ ሪፖርት ውድቅ መሆኑን ተከትሎ አሁንም ተቋሙ ችግሮችን ወደ ሌሎች አካላት ከመጠቆም ተቆጥቦ ግምገማውን ከራሱ እንዲጀምር እየተጠየቀ ነው፡፡   

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...