Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበችግር የተተበተበው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ

በችግር የተተበተበው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ

ቀን:

የደረቅ ቆሻሻ አዋጅ 513/99 በመላ አገሪቱ ለሚገኙ የከተማ አስተዳደሮች የደረቅ ቆሻሻ አያያዛቸውን በተመለከተ እንዲያቅዱና መሠረተ ልማት እንዲያመቻቹ ግዴታ ይጥልባቸዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ዓይነቱን ግዴታ ለመፈጸም በርካታ ተግዳሮቶች እንደተጋረጡ የደንና አካባቢ ሚኒስቴር የሕግና ደረጃዎች ተከባሪነት ዳይሬክቶሬት ይገልጻል፡፡

በአዳማ ከተማ አካባቢን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ለሁለት ቀናት በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሴሚናር ላይ የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያ አቶ ግርማ ገመቹ እንደሚሉት፣ ከተሞች ከገጠሟቸው ችግሮች መካከል የደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ ለመያዝ የሚያስችል አስፈላጊው መሠረተ ልማት ተሟልቶ አለመገንባቱ ይገኝበታል፡፡ የሕጎችን ተፈጻሚነት ለማረጋገጥና ተጠያቂነትን ለመፍጠር የሚያስችል አሠራርም የለም፡፡

አንዳንድ መሠረተ ልማቶች ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው የተገነቡ ቢሆንም የአስተዳደር ችግር በመኖሩ መስጠት የሚገባቸውን አገልግሎት ሳያከናውኑ ወይም ከአገልግሎት ጊዜያቸው በፊት ሥራ ያቆማሉ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በከተሞች ደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ላይ የሚሠሩ ተቋማት እንደ ከተሞቹ ስፋትና ቆሻሻ ባህሪ አሠራራቸው እንደሚለያይና  ደረጃቸውን ጠብቀው ይሠራሉ በሚል ታሳቢ ቢደረግም አሠራሩ ከደረጃ በታች ነው፡፡ ቆሻሻን በአግባቡ ሊይዙ የሚያስችላቸው አደረጃጀትም የላቸውም፡፡ በበርካታ ከተሞች ላይ ዘላቂነት ያለው የፋይናንስ ሥርዓት አልተዘረጋም፡፡

አንዳንድ ከተሞች የደረቅ ቆሻሻን ለሚሰበስቡ አካላት በውኃ ደረሰኝ (ቢል) ያስከፍላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሰብሳቢዎቹ ከቤተ ለቤት ገንዘብ እንዲሰበስቡ ያደርጋሉ፡፡ ይህም ወጥ የሆነ የፋይናንስ ሥርዓት እንዳይፈጸም አድርጓል፡፡

ቆሻሻን በአባወራ ወይም በቤተሰብ ደረጃ ለይቶ የማስወገድ ልምድ ዝቅተኛ መሆን፣ የሚወገደው ቆሻሻ መበስበስ፣ ማቀላቀል የሚቻለውንና የማይቻለው ቀላቅሎ እንዲወገድ ማድረግ፣ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የማድረጉ ወይም ሊጠቅም ወደሚችል ቁስ ቀልዝ (ማዳበሪያ) የመቀየር ልምድ አነስተኛ መሆን የችግሮቹ አካል እንደሆኑ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

የሚወገደውን ቆሻሻ ወደ ቁስ በመቀየር ቀድሞ የቆሻሻ መድፊያ ቦታዎችንና የመንገድ አካፋዮችን፣ እንዲሁም ፓርኮችን በቀልዝ የማልማት ሥራ በሐዋሳና በድሬዳዋ ከተሞች በቅርቡ ተጀምሯል፡፡ በአብዛኞቹ ከተሞች ግን ገና አልተጀመረም፡፡ ሆኖም አገሪቷ ከምታመነጨው ከ78 እስከ 80 በመቶ የሚሆነው ደረቅ ቆሻሻ ሊበሰብስ የሚችልና በቀላሉ ወደ ቀልዝ ተቀይሮ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ነው፡፡

ከተሞች የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የቅርብ ክትትልና ድጋፍ አለመኖር፣ የቴክኖሎጂ እጦት፣ በደረቅ ቆሻሻ ላይ ለሚሠሩ ግለሰቦች የደኅንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ከማሟላት አንጻር አቅርቦቱን የማመቻቸት ችግሮችም አሉ፡፡

ሚኒስቴሩ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በ2005 ዓ.ም. ያካሄደውን ጥናት ባለሙያው ዋቢ አድርገው እንዳብራሩት፣ በአገሪቱ በሚገኙ ከተሞች በዓመት የሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ ከ0.6 እስከ 1.8 ሚሊዮን ቶን ይሆናል፡፡ ይህም ማለት በሰው የሚመነጨው የቆሻሻ መጠን በቀን ከ0.17 እስከ 0.48 ኪሎ ግራም ይደርሳል፡፡

አሁን ተግባራዊ እየተደረገ ባለው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ስልት፣ ቆሻሻ ይመነጫል፣ ይጠራቀማል፡፡ ከተጠራቀመበት ቦታ በተወሰነ ደረጃ ይሰበሰባል፡፡ ከምንጩ የመቀነስ የመጀመሪያው ሥራ ቢሆንም በከተሞች እየተከናወና ያለው ሥራ በቂ እንዳልሆነ አቶ ግርማ ይናገራሉ፡፡

ከተሞች ከድሬዳዋና ሐዋሳ ልምድ በመውሰድ ደረቅ ቆሻሻን ለማዳበሪያነት የሚጠቀሙበትን ስልት ቢዘረጉ፣ ወጥ የሆነ የገንዘብ አሰባሰብ ሥርዓት ቢረኖር፣ በዘርፉ የተሰማሩ ማኅበራትና ተቋማት የሚጠናከሩበት መንገድ ቢመቻች፣ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ሥፍራዎችን ዘመናዊ ለማድረግ ከአገር ውስጥና ከውጭ ባለሀብቶች ጋር በጋራ ቢሠራ፣ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ቢቻልና በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚቻል ያነጋገርናቸው ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...