በአዲስ አበባ ከተማ በ311 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የኦሮሞ ባህል ማዕከል መጋቢት 16 ቀን 2007 ዓ.ም.በአዲስ አበባ ስታዲየም አካባቢ የተገነባው ማዕከል በ57 ሺሕ 100 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው ሥፍራ ላይ የከተመ ሲሆን አምስት የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ሙዚየም፣ ሲኒማ ቤት፣ የኦሮሞን ባህል የሚያሳዩ የሥነ ጥበባትና የቅርፃ ቅርፅ ውጤቶችም ተካቶበታል፡፡ ኦሕዴድ የተመሠረተበትን 25ኛ ዓመት ሲያከብር በይፋ የተመረቀው የባህል ማዕከሉ ግንባታ ዘጠኝ ዓመታትን ፈጅቷል፡፡ በምረቃው ላይ አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሙክታር ከድርን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራልና የክልል ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡ ምስሉ የሚያሳየው ከላይ (በግራ) ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የምርቃቱን ጥብጣብ ሲቆርጡ፣ ከላይ (በቀኝ) የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድር፣ የኦሮሞ ባህላዊ ልብስ የለበሱት (በግራ) አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን እና አቶ አዲሱ ለገሰ፤ የኦሮሞ ባህላዊ ጭፈራ በማዕከሉ ፊት ለፊት፡፡ (በታምሩ ጽጌ) ፎቶ በታምራት ጌታቸው