Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ይድረስ ለሪፖርተርተምሬ እንዳልተማርሁ የሚያደርጉ ችግሮች አስቸገሩኝ

ተምሬ እንዳልተማርሁ የሚያደርጉ ችግሮች አስቸገሩኝ

ቀን:

ፆታዬ ሴት፣ ዕድሜዬ 23 ዓመት ነው፡፡ የቤተሰቦቼ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ ስለሆነ ተገቢው ነገር ሳይሟላልኝ ከማደጌ ባሻገር ነገ ሰው እሆናለሁ በሚል ተስፋ ብዙ ችግሮችን ተቋቁሜ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በምማርበት ወቅት፣ የደረጃ ተማሪ ነበርኩ፡፡ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ባለው ደረጃ በመውጣት ከማሳለፌም በላይ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥቤም ጥሩ የሚባል ስለነበር ከልጅነቴ ጀምሮ እመኝ የነበረውን ሙያ ለመማር የሚያስችልኝን መስፈርት አሟልቼ ነበር፡፡

መማር የምፈልጋቸውን የትምህርት መስኮች በቅደም ተከተል በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ፎርም ላይ ብገልጽም፣ በምን ምክንያት እንደሆነና መለኪያው ምን እንሆነ ሳይገባኝ ባልመረጥኩት ሙያና ዩኒቨርሲቲ መደልደሌ ዕድሌን ሁሉ አበላሽቶብኝ ዛሬ ላለሁበት ችግር መንስዔ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡

ይሁን እንጂ የተመደብኩበት ዩኒቨርሲቲ ከሚሰጣቸው ኮርሶች አንዱን መርጦ መማር የግድ ስለነበር፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ቋሚ የአየር ጊዜ ተሰጥቶት ተጋኖ ስለሚወራለት የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገት ትዝ ስላለኝ ብቻ ውስጡን ሳላውቀው (Eco-truism & biodiversity conservation) የሚባል የትምህርት ዘርፍ፣ ያውም በሰው ኃይል ገበያው ላይ የማይታወቅ አዲስ የትምህርት መስክ መርጬ ተማርኩኝ፡፡ ትምህርቴን ሳጠናቅቅ አጠቃላይ የመመረቂያ ነጥቤም 3.50 ነበር፡፡

- Advertisement -

ተመርቄ እንደወጣሁ ተደራጅቶ ሥራ መፍጠር ይቻላል ይባል ስለነበር ስድስት ሆነን በጥቃቅንና አነስተኛ ለመደራጀት ተሰባሰብን፡፡ ለገበያ ጥናት እንቅስቃሴ በጀመርንበት ወቅት ጓደኞቼ በሙሉ በተማሩትበት የሙያ መስክ እየተቀጠሩ ሲሔዱ፣ በእኔ ሙያ መስክ ግን አንድም ማስታወቂያ ስለማይወጣ ብቻዬን ቀረሁ፡፡ ሌላ አማራጭ በሐሳብ ሳፈላልግ ቆየሁና ለትምህርት ያለኝ ስሜት ሳይቀዘቅዝ የቀን ሥራ እንኳ እየሠራሁ በማገኘው ሳንቲም በጎንዮሽ ሙያ በማስተርስ ደረጃ ሰልጥኜ በጥሩ ውጤት ተመርቄ ጓደኞቼ የደረሱበት ደረጃ ለመድረስ እልህ ውስጥ ገባሁ፡፡

በዚሁ መሠረት ዶክመንቶቼን ይዤ ለመመዝገብ ወደ አንድ ዩኒቨርሲቲ ሳመራ፣ የወጪ መጋራት ዕዳ ካልከፈልሽ መማር አትችይም ተባልኩ፡፡ በግል ኮሌጅ ተመዝግቤ በርቀት ተምሬ በወቅቱ የሚፈልገውን ማስረጃ ለማግኘት ያደረኩት ሙከራም በተመሳሳይ ሁኔታ ከሸፈብኝ፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ገንዘብና የሚረዳኝ ዘመድ በማጣቴ ብቻ ለመማርም ሆነ ለመሥራት እግዚአብሔር የሰጠኝ የተፈጥሮ አቅም እያለን፣ እጅ እግሬና አዕምሮዬ ጭምር ታስሮ ብዙ ውጤታማ ሥራ መሥራት የምችልበት ዕዳሜዬ በከንቱ እየባከነብኝ ችግር ውስጥ እገኛለሁ፡፡

ሥራ ፈጥሬ ውጤታማ ለመሆን በተደጋጋሚ ሞክሬ አልተሳካልኝም፡፡ የወጪ መጋራት ዕዳዬን ከፍዬ የማይረባ ሙያ መማር ወይም በሌላ አማራጭ የሚያስቀጥረኝ ዘመድ እስከሌለ ድረስ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቼ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ዓረብ አገር ለመጥፋት ሳስብም፣ ከበስተጀርባው ሞትና መከራ እንዲሁም ስቃይ መኖሩን አስባለሁም፡፡ በግማሹ ደግሞ ስኬት ሊኖረው ይችላል በሚል ተስፋ ተፅናንቼ አቋም እንዳልይዝ ለደላላ የሚከፈለው ገንዘብም ከአቅሜ በላይ ሆነ፡፡ ታዲያ የስኬት በሮች ሁሉ ለእኔ ዝግ ከሆኑ ምን ማድረግ እችላለሁ? አዕምሮዬን ማረጋጋት የምችልበት መላ አጥቼ እየባዘንሁ እገኛለሁና ለዚህ መፍትሔ ያለው አለሁ ቢለኝ ደስታዬ ወደር የለውም፡፡

(DN ND፣ ከኦሮሚያ)

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...