Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየታንዛኒያ ፓርላማ የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በሙሉ ድምፅ አፀደቀ

የታንዛኒያ ፓርላማ የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በሙሉ ድምፅ አፀደቀ

ቀን:

የታንዛንያ ፓርላማ የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA) በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፡፡

ከአሩሻ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ የታንዛኒያ ብሔራዊ ሸንጎ የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ያለአንድ ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ አፀድቋል፡፡

መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. የተሰበሰበው የአገሪቱ ሕግ አውጪ ምክር ቤት፣ በውኃ ሚኒስትሩ ጁማኔ ማገምቤ የቀረበውን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በሙሉ ድምፅ ያፀደቀው፣ በቀጥታ በአገሪቱ ቴሌቪዥን በተላለፈ ፕሮግራም እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እ.ኤ.አ. በ2010 የተረቀቀውና አሥሩ የተፋሰስ አገሮች በተፋሰሱ ዙርያ ያደረጉት ድርድር ውጤት የሆነው ይኼው የውኃ ስምምነት፣ አሮጌዎቹ የቅኝ ግዛት ስምምነቶች (ግብፅና ሱዳን የተስማሙባቸው) የሚተካ ብቸኛ የሕግ ሰነድ ነው፡፡ እስካሁን ታንዛኒያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳና ሩዋንዳ) ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡ ግብፅና ሱዳን ለመፈረም ፈቃደኛ አለመሆናቸው ይታወሳል፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲን በመወከል የፓርላማ አባል የሆኑት ፖውለን ጌኩል ይህንን በተመለከተ፣ ‹‹ግብፅና ሱዳን ያላንዳች ተቀናቃኝ ውኃውን ሙሉ ለሙሉ ሲጠቀሙበት ማየት ፍትሐዊ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹በተለይ ታንዛንያ ለተፋሰሱ [ነጭ ዓባይ] 28 በመቶ እያመነጨች 0.1 በመቶ ብቻ ጥቅም ላይ ማዋሏ አሳፋሪ ነው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የፓርላማ አባሏ የቪክቶሪያ፣ የታንጋኒካና የንያሳ ሐይቆችን ጨምሮ አገራቸው ካሏት የውኃ ሀብቶች መጠቀም ሳትችል በምግብ እጥረት መሰቃየቷ አሳፋሪ እንደሆነም አክለዋል፡፡

ገዥውን ፓርቲ በመወከል የፓርላማ አባል የሆኑት ሒልደር ንጎየ ታንዛኒያ ከየትኛውም አገር ቀድማ ሕጉን ማፅደቅ እንደነበረባት ገልጸው፣ ‹‹እኛ የታችኛው ተፋሰስ አባል አገሮች ወንድሞቻችን ውኃውን እንዳይጠቀሙ እየከለከልን አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ታንዛንያ ወንዙን ጥቅም ላይ ለማዋል ስትፈልግ ግብፅን ስትለምን መኖሯ አግባብ አይደለም፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...