‹‹ዜጋ››
በአዲስ አበባ የግብረሰዶማውያን እውነተኛ ታሪኮችን የሚያስቃኘውና የሃይማኖት አባቶችንና የሌሎችንም አስተያየት ያካተተው ‹ዜጋ› የተሰኘው መጽሐፍ ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ ስምንት ሰዓት በግዮን ሆቴል ይመረቃል፡፡
የመጽሐፉ ደራሲ ጋዜጠኛ ፍሬወይኒ ግደይ ስትሆን፣ መጽሐፉ 169 ገጾች አሉት፡፡ ዋጋውም 50 ብር ከ60 ሳንቲም ነው፡፡
*******
‹‹በቀናት መካከል››
ኤፍሬም ፊልም ፕሮዳክሽን ‹‹በቀናት መካከል›› የተሰኘ አዲስ ተከታታይ ድራማ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ሊያቀርብ ነው፡፡ ድራማው ከፊታችን ሚያዝያ 9 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር ዓርብ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ይቀርባል፡፡
*****
ምርቃት
ወጋገን ኮሌጅ በቴአትር ጥበባት፣ በፊልም ጥበባት በአካውንቲንግና በአይሲቲ ሙያዎች ያሠለጠናቸውን ሠልጣኞች ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ.ም. በዓለም ሲኒማ አዳራሸ ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 6፡00 ሰዓት ያስመርቃል፡፡