Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልባህር የተሻገረ ጥበብ

ባህር የተሻገረ ጥበብ

ቀን:

ባለፈው ሳምንት ተመርቆ ሥራ የጀመረው የኦሮሞ ባህል ማዕከል በጎብኝዎች ተጨናንቋል፡፡ ባህል ማዕከሉን ለመጎብኘት በቦታው የተገኙ ግለሰቦች ማዕከሉ ከተከፈተ የመጀመርያ የሆነውን ዐውደ ርዕይ የመመልከት ዕድል አግኝተዋል፡፡

ሥዕሎቹ የታዋቂው ሜክሲኳዊ ሠዓሊ ሊዎፓርዶ ፍሎሬዝ ሥራዎች ናቸው፡፡ ሠዓሊው 84 ዓመታቸው ሲሆን፣ በእርጅና ምክንያት ወዲህ ወዲያ አይሉም፡፡ መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. በማዕሉ የተከፈተውን ዐውደ ርዕይ ለመታደምም አልቻሉም፡፡ በመሆኑም ሥዕሎቹን ወደ ኢትዮጵያ ያመጧቸው የሊዎፓርዶ ባለቤት ደሎሪየስ አልማታ ፍሎሬዝ ናቸው፡፡

የሠዓሊው ሥራዎች ከሜክሲኮ ወጥተው በአህጉረ አፍሪካ ለዕይታ ሲቀርቡ ኢትዮጵያ የመጀመርያዋ አገር ናት፡፡ የሠዓሊው ባለቤት አልማታ ለሪፖርተር እንዳስረዱት፣ ሊዎፓርዶ በዐውደ ርዕዩ መገኘት ባይችሉም ሥራዎቻቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በመታየታቸው ደስተኛ ናቸው፡፡ የሥዕል ሥራዎቹ እ.ኤ.አ. ከ1960ዎቹ እስከ 2003 ያሉትን የሚያካትቱ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ በኋላ ወደ አውሮፓና እስያ ይሄዳሉ፡፡

የሠዓሊው ሥራዎች በአውቶመስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዘ ስቴት ኦፍ ሜክስኮ  ውስጥ በስማቸው በተሰየመ ሙዝየም ይገኛሉ፡፡ የሙዝየሙ ኃላፊ ኢቤት ቲኖኮ እንደምትለው፣ ሊዎናርዶ በሜክሲኮ ከተለመደው አሳሳል ውጭ በመሥራት ይታወቃሉ፡፡ ከነዚህ ታሪካዊ ሥራዎቻቸው ውስጥም 21ዱ በዐውደ ርዕዩ እንደተካተቱ ገልጻለች፡፡ ሊዎፓርዶ በሥራ ላይ ሲሆኑ፣ ሜክሲኮ ውስጥ ስምንት ሜትር በ12 ሜትር በሆነ ሸራ ላይ የጥበብ ሥራቸውን እያኖሩ እንደሚገኙም አክላለች፡፡

 ዩኒቨርሲቲው ባለፈው ዓመት የሜክሲኳዊ ፎቶ አንሺ ሥራዎችን ኢትዮጵያ ውስጥ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡  የዐውደ ርዕዮቹ ዓላማ በአገሮቹ መካከል የባህል ትስስር ለመፍጠር መሆኑን ቲኖኮ ተናግራለች፡፡

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዩሳ ዐውደ ርዕዩ የሜክሲኮን ጥበብ ለኢትዮጵያውያን ከማሳየቱ በተጨማሪ ባህል ማዕከሉን ሜክሲኳውያን እንዲጎበኙት መንገድ ከፍቷል ብለዋል፡፡ ማዕከሉ ከተከፈተ በቀናት ልዩነት ዐውደ ርዕይ ማስተናገድ እንደጀመረ ሁሉ በቀጣይም በርካታ ጥበባዊ ሥራዎች እንደሚቀርቡበትም አስረድተዋል፡፡

ለአንድ ወር ያህል ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ በሚቆየው ዐውደ ርዕይ መክፈቻ ላይ የተገኙት አቶ ጌቱ፣ ለሊዎፓርዶ ባለቤት አልማታ፣ የኦሮሞ ባህላዊ ዕቃ አበርክተዋል፡፡

        

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...