Sunday, December 8, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአማራና የትግራይ ሕዝቦች ውይይት ነገ ይጀመራል

የአማራና የትግራይ ሕዝቦች ውይይት ነገ ይጀመራል

ቀን:

spot_img

የአማራ ክልልና የትግራይ ክልል የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት መድረክ ቅዳሜ ኅዳር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ሊካሄድ እንደሆነ የአማራ ክልል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በግል ይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ገለጹ፡፡

አቶ ንጉሡ “የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሕዝብ ለሕዝብ መድረክ በመፍጠር በአብሮነትናአንድነት ላይ ምክክር ለማካሔድ ባቀደው መሠረት በነሐሴ ወር በመቀሌ ተካሂዶ የነበረው የአማራና የትግራይ ክልሎች ሕዝቦች የጋራ መድረክ ቀጣይ ክፍል በታሪካዊቷና የከተሞች እናት በመባል በምትታወቀው ጎንደር ከተማ ይጀመራል፡፡ምክክር መድረኩ እስከዳር 10 ቀን 2010 .. የሚቆይ ሲሆን፣ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 500 ያህል የሃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ምሁራን፣ አመራሮችና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በምክክር መድረኩ ላይ ለመታደም ወደ ጎንደር በመጓጓዝ ላይ ናቸው፤” በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

ከአማራ ክልል ብቻ 800 ተሳታፊዎች የሚገኙበት ይህ መድረክ ከሁለቱም ክልሎች 1300 ያህል ተሳታፊዎች ወደ ጎንደር ከተማ ዛሬ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

በነገውለት በሚጀመረው የምክክር መድረክ ላይየመወያያ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ይደረጋል፤” ሲሉ ኃላፊው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

ከሁለት ሳምንታት በፊት በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ የተመራው ልዑክ የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት ለማርደግ በባህር ዳር ከተማ ተገኝተው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከምክክርና ከድርድር ውጪ ምን ዓይነት አማራጭ ይኑረን?

በዘውዳለም መንገሻ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ነፃነትና ሰንሰለት

(ክፍል አንድ) በታደሰ ሻንቆ 1) ‹‹ውስጣዊ ሰንሰለቶች እንዳሉ ሁሉ ውጫዊ ሰንሰለቶችም...

ገበያውን ሊያረጋጉ የሚችሉ አዳዲስ መፍትሔዎችን ማምጣት ያስፈልጋል!

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎንፌ (ዶ/ር) በሕዝብ...

አዲሱ የሕንፃ አዋጅ ‹ድርጅት ተኮር› ሳይሆን ‹ባለሙያ ተኮር› ተደርጎ መዘጋጀት አለበት የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር

የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር በቀድሞ የሕንፃ አዋጅ የነበረውን ‹‹ባለሙያ ተኮር››...