ጥሬ ዕቃዎች
ግማሽ ኪሎ ግራም የበሬ ሥጋ (የእግሩ ቢሆን ይመረጣል)
1 ራስ ቀይ ሽንኩርት
2 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
2 ራስ ካሮት
5 ፍሬ ቲማቲም
200 ግራም ብሮኮሊ
6 ጭልፋ የአትክልት ማጣፈጫ ሾርባ
50 ሚሊ ሊትር ወይን ጠጅ (1 ቡና ሲኒ)
1 የሾርባ ማንኪያ ደረቅ የጥብስ ቅጠል
(1/2) ግማሽ ብርጭቆ ቅንጬ
(1/2) ግማሽ የሻይ ማንኪያ ሚጥሚጣ
5 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
ጨውና ቁንዶበርበሬ
አዘገጃጀት
- ሥጋውን በመካከለኛ መጠንና በአራት ማዕዘን መቆራረጥ፤
- ቀይና ነጭ ሽንኩርቱን በደቃቁ መክተፍ፤
- ካሮቱንና ቲማቲሙን በደቃቁ መክተፍ፤
- ብሮኮሊውን ገነጣጥሎ መክተፍ፤
- ቅንጬውን በደንብ ማጠብ፤
- ተለቅ ባለ ድስት ዘይት ማጋልና ሥጋውን መጥበስ፤
- ከድስት ውስጥ ሥጋውን አውጥቶ ሥጋው በተጠበሰበት ዘይት ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ካሮትና የጥብስ ቅጠል በደንብ ማቁላላት፤
- ቲማቲሙን ጨምሮ ለአምስት ደቂቃ አብስሎ የተጠበሰውን ሥጋ እንደገና ወደ ድስት መጨመር፤
- ቅንጬውንና ወይን ጠጁን ወደ ሥጋ ጨምሮ እንደገና ማብሰል፤
- የሾርባ ማጣፈጫውን ጨምሮ ለ20 ደቂቃ ማብሰል፤
- ብሮኮሊውን ጨምሮ ለሌላ አምስት ደቂቃ ማብሰል፤
- ሚጥሚጣ፣ ጨውና ቁንዶበርበሬ ጨምሮ ማውረድ፡፡
- ጆርዳና ኩሽና ‹‹የምግብ አዘገጃጀት›› (2007)