ፊስአልጎስ ስለ ከራድዮን እንዲህ ይላል፤ የዚህ ወፍ ሁለንተናው ነጭ ስለሆነ በፀጉሩ ላይ ምንም ጥቁር የለበትም፤ እርሱም በነገሥታት ቤት ውስጥ ይገኛል፡፡
በጥኑ ደዌ ሰውነቱ የታመመና ዓይኖቹን የታወረ ሰው ካለ፣ የዚህ ሰው ሕመሙ ለሞት የሚያደርሰው ከሆነ ሰው ሁሉ እንደሚሞት እስኪያውቅ ድረስ ከራድዮን የታመመውን ሰው አይመለከተውም፤ ሕመሙ ለሞት የማያደርሰው ከሆነ ፊቱን ወደ እርሱ መልሶ ያየዋል፡፡ ያን ጊዜ የሰውየውን ሕመም ተቀብሎ ወደ አየር ይበርራል፡፡ የፀሐይ ግለት ሕመሙን እስኪያቃጥለው (እስኪፈጀው) እና ከራድዮንና ሕመምተኛው በአንድ ላይ ተፈውሰው እስኪድኑ ድረስ፡፡
- ሮዳስ ታደሰ ‹‹መጽሐፈ ፊስአልጎስ በግእዝና በአማርኛ›› (2009)