በደረጀ ጠገናው
ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፕሬዚዳንትና ለሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ ለመሰየም፣ ለሐሙስ ኅዳር 14 ቀን 2010 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ በጽሕፈት ቤቱ ወሰነ፡፡
ለአስቸኳይ ስብሰባው የሚሆን አዳራሽ ለመከራየት ፌዴሬሽኑ ስፖንሰር እያፈላለገ እንደሆነ፣ ጥቅምት 30 እና ኅዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ለተካሄደው ጉባዔ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣ ለማወቅ ለችሏል፡፡
በፊታችን ሐሙሱ አስቸኳይ ስብሰባ በአፋር ክልል የሚካሄደው ምርጫ የአስመራጭ ኮሚቴ መሰየም፣ ለክልል አንድ ብቻ እንዲሆን የተወሰነውን የዕጩ ተወዳዳሪዎች ቁጥር ገደብ እንዲቀር ይደረጋል ተብሏል፡፡