Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየፒኮክ ፓርክ የልማት ተነሺዎች በአግባቡ እየተስተናገድን አይደለም አሉ

የፒኮክ ፓርክ የልማት ተነሺዎች በአግባቡ እየተስተናገድን አይደለም አሉ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ የመልሶ ማልማት ፕሮግራም ከሚያካሂድባቸው ቦታዎች የሚነሱ ነዋሪዎች ፍላጎታቸው ሳይሟላ እንደማይነሱ ይፋ ቢያደርግም፣ ቦሌ ከሚገኘው ማዕከላዊ ፓርክ (ፒኮክ መናፈሻ) የሚገኙ ነዋሪዎች ፍላጎታቸው ሳይሟላ እንዲነሱ እየተደረገ መሆኑን ገለጹ፡፡

የፒኮክ መናፈሻ የልማት ተነሺዎች መጋቢት 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ቅሬታቸውን በደብዳቤ ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎች የመረጡት ኮሚቴ ለከንቲባው በጻፈው ደብዳቤ እንደገለጸው፣ ለአካበቢው አንጋፋና ለረጅም ዓመታት የኖሩ 30 አባወራዎችን ከሌሎች ነጥሎ በክፍለ ከተማ ይዞታዎች መስተንግዶ ፕሮጀክት በመመርያ ቁጥር 18/2006 መሠረት እንደማይስተናገዱና ንብረታቸውንም እንዳያነሱ ወስኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኮንዶሚንየም መኖሪያ ቤት የመረጡ የልማት ተነሺዎች 176 አባወራዎች ናቸው፡፡ እነዚህ አባወራዎች ቦሌ ቡልቡላ ሳይት እንደሚሰጣቸው ተገልጾላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን መጋቢት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ዕጣ ይወጣል ሲባል ቤቶቹ በተለያዩ ሳይቶች እንደሚገኙ ተገልጾላቸዋል፡፡

ዕጣ ለማውጣት ለተሰበሰበው ሕዝብ የተገለጸው የኮንዶሚንየም ሳይቶች በመበርከታቸውና ቀደም ሲል የተገባው ቃል ቦሌ ቡልቡላ በመሻሩ ከፍተኛ ቅሬታ መፈጠሩን በደብዳቤው ተገልጿል፡፡

‹‹የሳይቶቹ መበርከት የዕድሜ ልክ ማኅበራዊ ግንኙነቶቻችንን የሚያቋርጥ ነው፤›› ሲሉ የኮሚቴው አባል አቶ ደምለው ካምበው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

አቅመ ደካሞችና የዕድሜ ባለፀጎች በመኖራቸው ተለያይቶ መኖር አስቸጋሪ ይሆናል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪና የልማት ተነሺ የሆኑት ወ/ሮ ዓይናለም ደመቀ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ1940 ዓ.ም. የተመሠረተው አንበሳ ግቢ ፓርክ ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት ወደ ቦሌ ፒኮክ መናፈሻ የማዞር ዕቅድ አውጥቶ እየሠራ ይገኛል፡፡

ይህንን ፓርክ ለማስፋት በርካታ ነዋሪዎች ይነሳሉ፡፡ ተነሺዎቹ ነባር ነዋሪዎች ለልማት ሲባል መነሳታቸውን ቢደግፉም፣ ማግኘት ያለባቸውንና መንግሥት ቃል የገባላቸውን ሊያከብር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በያዘው ዕቅድ መሠረት፣ ከዚህ በኋላ ከመልሶ ማልማት ቦታዎች የነዋሪዎችን ፍላጎት ሳያረካ እንደማያነሳ በቅርቡ በተካሄደው ምክር ቤት ጉባዔ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...