Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ሲኒማ አምፒር ድሮና ዘንድሮ

ትኩስ ፅሁፎች

ከቆሼ ሰፈር  ሟች ወገኖች  ለእኛ  የተላከ መልዕክት

“ሞቱ” “ሞቱ” አትበሉ
ከሰው መንጋ  ሸሽተን…… የተጠለልንበት አፈሩ ሳይከዳን፣
ሳይከዳን  ነፋሱ…. ሳይከዳን  ተፈጥሮ፣
ያኔ ነው……..
ያኔ ነው የሞትነው ገና ድሮ ድሮ፣

ሰው በምድር ሲኖር ስንትዜ ይሞታል ……ስንት ሞት ነው ያለው …
ከሞት ጋር ተፋቅረን፣ ከሞት ጋር ተጋብተን
ከሞት ጋር ተዋልደን  አንተ  ትብስ  አንቺ ብለን  ተባብለን
ከመላመድ ብዛት እኛ እሱን  ንቀነው
እሱም እኛን ንቆን በ “ፍቅር” እንዳልኖርን፣
 “ሞቱ” “ሞቱ” አትበሉ ….
አቦ “አረፉ” በሉ አይደላንም ቃሉ፣
ከምንዱባን  ሕይወት  ከጉስቁል ኑሯችን…እፎይ  አረፍን ስንል
እልል እንደማለት…ፍሪዳ እንደመጣል
ሻምፓኝ እንደ መክፈት፣
 “ሞቱ” “ሞቱ” እያሉ የምን ሙሾ ማውረድ
የምን ደረት መድቃት…

ዛሬ እንኳ እስኪ ስሙን…
ማይኩን ልቀቁልን….
ይሰማ ድምፃችን ወግ ደርሶን እናውራ ፣
ምትሃተ ፍቅራችን በውል እንዲሠራ
 አረፉ ብላችሁ እርገጡ ዳንኪራ
ያዙ  ካቲካላ…. ወይ ቢሻችሁ ቢራ..
ደንሱ እልል በሉ….
አለያ ግን ተዉት ኖረን እንደምናውቅ “ሞቱ” “ሞቱ” አትበሉ ….
 “አብረን ዝም እንበል” እንዳለው ገጣሚው
እኛ ዝም ብለናል እናንተም ዝም በሉ፡፡
                                    ሙ.ቢ (7/7/09 ዓ.ም.  አዲስ አበባ)

***

የጀግኖች መታሰቢያ ሐውልት ላይ የሸናው ታዳጊ ታሰረ

በስኮትላንዷ ፋይፍ ከተማ በጦርነት መስዋዕት ለሆኑ ጀግኖች መታሰቢያነት በቆመ ሐውልት ላይ የሸና የ14 ዓመት ታዳጊ ታሰረ፡፡

በሞናስትሪ ጎዳና ላይ በሚገኘው ሐውልት ላይ የሸናው ታዳጊ ከማኅበረሰብ ያፈነገጠ ባህሪ በማሳየቱ ሲታሰር፣ ከእሱ ጋር የነበሩና በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉ አሥር ሰዎችም ቃላቸውን እየሰጡ መሆኑ ቢቢሲ አስፍሯል፡፡

***

አሜሪካ ከአውሮፕላን መንገደኞች ጋር ኤሌክትሮኒክስ እንዳይጫን አገደች

አሜሪካ ሙስሊም ከሚበዛባቸው የመካከለኛው ምሥራቅ ስምንት አገሮች የሚነሱ በረራዎች ከእጅ ስልክ በስተቀር፣ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በሻንጣ አድርገው ተሳፋሪዎች ከሚቀመጡበት የአውሮፕላኑ ክፍል መግባት አይችሉም፡፡ ሆኖም የተፈተሸ ሻንጣ በሚቀመጥበት የአውሮፕላኑ ዕቃ ክፍል ማስገባት ይችላሉ፡፡

የደኅንነት ሥጋትን ከመቀነስ አንፃር ዕገዳውን የጣለችው አሜሪካ፣ በላፕቶፕ፣ በካሜራ፣ በታብሌት፣ በዲቪዲ ማጫወቻ፣ በጌሞችና በሌሎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ቦንብ ተደብቆ ሊገባ ይችላል ብላለች፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ በዕገዳው ሞሮኮና ቱርክ፣ ዮርዳኖስና ግብፅ፣ ኩዌት፣ ኳታርና ሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ አየር መንገዶች የሚጎዱ ሲሆን፣ ከእነዚህም ኢሚሬትስ፣ ኢትሃድ ኤርዌይስ፣ ኳታር ኤርዌይስ፣ ሮያል ኤር ማሮክ፣ ተርኪሽ ኤርላያንስ፣ ኢጅፕት ኤርዌይስ፣ ሮያል ጆርዳንና ሳዑዲ ዓረቢያን ኤርላይንስ በዕገዳው ይጎዳሉ፡፡

****

የውሻ ነገር

ውሻ ቢደበድቡትና ቢያባርሩት እስኪሞት ድረስ ከጌታው ቤት አይለቅም (ተሰናዕዎቱ) መስማማቱ ይህ ነው፡፡ ውሻ ቢቆጡት (ውጣ ቢሉት) ቁጣውን በትዕግስት ተቀብሎ ይሄዳል እንጂ ጠሉኝ ተቆጡኝ ብሎ ጌታውን አይንቅም (አይጠላም) ፍቅሩና ልቦናው ይህ ነው፡፡

ውሻ ውጣ ሲሉት ይወጣል፣ ና ሲሉት ይመጣል፡፡ ትሕትናው ነው፡፡ ውሻ በመጮኽ እየዞረ የጌታውን ቤት ተግቶ ይጠብቃል ማመስገኑ ነው፡፡ ውሻ ምንም እንኳ ምግቡን ባይሰጡት (አስራቡኝ አስጠሙኝ)  ብሎ የጌታውን ቤት ለቆ መሄድ የለበትም፤ ምግቡን መነሳት ቀርቶ ቢመቱት ቢደበድቡት እንኳ ወደ ሌላ አይሄድም፡፡ ተስፋው ይህ ነው፡፡

ውሻ ጌታውን ሲያይ ጅራቱን ይቆላል፣ ራሱን እየቆላመመ ጌትየውን ይተሻሽዋል፡፡ ያቆላምጠዋል፡፡

  • ሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ «አንጋረ-ፈላስፋ» (1953)
  •  

‹‹የንጉሣውያን ዘር አሳ ነው››

በ1543 ዓ.ም. በእንግሊዝ አገር አሳ ነባሪ፣ ‹‹የንጉሣውያን ዘር አሳ ነው›› ተብሎ ታውጆ ነበር፡፡ በዚያም አዋጅ ውስጥ ማንኛውንም አሳ ነባሪ የሚይዝ አሳ አጥማጅ፣ አሳ ነባሪውን እንደያዘ የአሳ ነባሪውን ራስ ለንጉሡ፤ ጭራውን ደግሞ ለንግሥቲቱ መላክ ነበረበት፡፡

  • ጳውሎስ ኞኞ «ሁለተኛው አስደናቂ ታሪኮች» (1965)
  •  

ሲኒማ አምፒር ድሮና ዘንድሮ

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች