Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለ2024 ኦሊምፒክ ዝግጅት ሎሳንጀለስና ፓሪስ ተፋጠዋል

ለ2024 ኦሊምፒክ ዝግጅት ሎሳንጀለስና ፓሪስ ተፋጠዋል

ቀን:

  • የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መጋቢት 23 አዲስ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ይመርጣል

የ2024 የበጋ ኦሊምፒክና ፓራ ኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የአሜሪካዋ ሎሳንጀለስና የፈረንሣይዋ ፓሪስ ‹‹እኔ እመጥናለሁ›› ፍጥጫ ቀጥሏል፡፡ የጀርመኗ ሐምቡርግ፣ የጣሊያኗ ሮምና የሐንጋሪዋ ቡዳፔስት ለማስተናገድ ያቀረቡትን ጥያቄ ሰርዘዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) ሕግ አንቀጽ 33 ንዑስ አንቀጽ 2 አስገዳጅ ሁኔታዎች እስካልገጠሙ ድረስ፣ የኦሊምፒክ ጨታዋዎችን ለማስተናገድ ጥያቄ ለሚያቀርቡ አገሮች የፉክክሩ መድረኩ ከሰባት ዓመት በፊት ቀደም ብሎ ክፍት ሊደረግላቸው ይገባል፡፡

የአይኦሲ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ፣ የ2024 እና የ2028 የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን የሚያስተናግዱ ከተሞች መስከረም 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ፔሩ ላይ በሚደረገው የአይኦሲ መደበኛ ስብሰባ ይፋ እንደሚያደርጉ ነው በመግለጫው የተገለጸው፡፡ ይሁንና የ2024 ኦሊምፒክን ለማስተናገድ በብቸኝነት የቀረቡት ሎሳንጀለስና ፓሪስ የ2024ቱን መስተንግዶ የማይሰጣቸው ከሆነ ግን፣ ለ2028ቱ ጥያቄ የማቅረብ ፍላጎቱ እንደሌላቸው መግለጫው ያብራራል፡፡

የአይኦሲ ፕሬዚዳንት በበኩላቸው ሁለቱ አገሮች የያዙት አቋም ትክክል እንዳልሆነ በመግለጽ፣ ጉዳዩን አጥንቶ የውሳኔ ሐሳብ የሚያቀርብ አካል ማቋቋማቸውም ታውቋል፡፡

የኮሚቴው አባላትም ተጠሪነቱን ለአይኦሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆኖ፣ አውስትራሊያው ጆን ኳታስ፣ ቱርካዊው ዩጋር አርጋነር፣ ቻይናዊ ዩዛኮንግና ስፔናዊ ጆን አንቶንዮ ሳማራንሽ መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በሚያደርገው ጉባኤ፣ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴውን ለቀጣዩ አራት ዓመት የሚያስተዳድሩ በዕጩነት 15 ተወዳዳሪዎች ስም ዝርዝር መታወቁን የኦሊምፒክ ኮሚቴው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...