Thursday, February 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአፍሪካ የቼስ ሻምፒዮና በጅማ ከተማ ቅዳሜ ይጀመራል

የአፍሪካ የቼስ ሻምፒዮና በጅማ ከተማ ቅዳሜ ይጀመራል

ቀን:

በኢትዮጵያ የቤት ውስጥ ከሚከናወኑ ስፖርታዊ ክንውኖች ውስጥ ቼስ ተጠቃሽ ነው፡፡ በቀድሞ የኢትዮጵያ ነገሥታትም ተወዳጅ የጨዋታ ዓይነትም እንደነበር መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ የሠንጠረዥ ጨዋታ በማለትም እንደሚጠሩ ይነገራል፡፡ ምንም እንኳ የስፖርቱን ተዘውታሪነት ለመጨመር ባይቻልም ለአዛውንቶች፣ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የዕረፍት ጊዜ መዝናኛነት ተመራጭ እየሆነም ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን የተለያዩ ውድድሮችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ በዚህም መሠረት የዘንድሮው የአፍሪካ ቼስ ሻምፒዮናና የዓለም ሻምፒዮና ማጣሪያ የዞን አራት ሁለት ውድድር በመጪው ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በጅማ ከተማ ይካሄዳል፡፡

ውድድሩ በተለያዩ የምሥራቅና የሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ይካሄድ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ እንደምታዘጋጅ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 የአፍሪካ አገሮች ማለትም ግብፅ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳና ሲቬልስ ተሳታፊ ሲሆኑ፣ ከ100 በላይ ሴትና ወንድ ተወዳዳሪዎች ይካፈሉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ የኢንተርናሽናል ማስተር ማዕረግና የገንዘብ ሽልማት ከመበርከቱ በተጨማሪ አፍሪካን ወክለው በዓለም የቼስ ሻምፒዮና ላይ እንዲካፈሉ ይደረጋል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያም በዚህ ሻምፒዮና ብዛት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን በማሳተፍ ተጠቃሚ እንደምትሆንም ተገልጿል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በክልል ከተማ ላይ ሻምፒዮናው መካሄዱ ለከተማው ስድስት ተጫዋች ዕድል መፍጠሩ ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በወንዶች ምድብ በጠቅላላው አሥራ አራት፣ በሴቶች ምድብ ስምንት በጠቅላላው ሃያ አራት ተወዳዳሪዎችን እንደምታሳትፍ የፌዴሬሽኑ መግለጫ ያስረዳል፡፡

በጅማ ከተማ የሚገኙት የቼስ ተወዳዳሪዎች በተለያየ ጊዜ ዞናቸውንና ክልልላቸውን በመወከል አመርቂ የሚባል ውጤት ማምጣታቸው ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ ላደረገችው ውድድር አስተዋጽኦ ማድረጉ ተብራርቷል፡፡

ቀድሞ በነበሩት ውድድሮች ግብፅ በተደጋጋሚ በማሸነፍ ዞኑን በበላይነት ስትመራ ኡጋንዳና ታንዛኒያ የሚከተሏት አገሮች ናቸው፡፡ በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ የተሻለ ውጤት እንደምታመጣ ግምት ካገኙ አገሮች ተጠቅሳለች፡፡

በጅማ በቼስ ስፖርት ከ1970ዎቹ ጀምሮ ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚታይባት ከተማ እንደሆነችና ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ የጅማ ቼስ ፌዴሬሽን ተቋቁሞ በያዝነው ዓመት የአገር ውስጥ ውድድሮችን ሊያስተናግድ መቻሉ ጭምር በመግለጫው ተካቷል፡፡

ቼስ በዓለም ላይ ከሚገኙ የቤት ውስጥ ስፖርቶች አንዱና ከ500 ሚሊዮን በላይ አዘውታሪዎች ያሉት ሲሆን፣ በየትኛውም ዕድሜ ላይ ያሉ ሰዎች ሊያዘወትሩት የሚችሉት አዕምሮን ለማበልፀግ የሚዘወተር የስፖርት ዓይነትም እንደሆነ ይታመናል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...