Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትደደቢት ከአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወጣ

ደደቢት ከአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወጣ

ቀን:

በውድድር ዓመቱ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የአገሪቱ ተወካይ የነበረው ደደቢት ተሳትፎው በናይጄሪያዊው ዋሪ ዎልቭስ ተገታ፡፡ በመድረኩ ሲሳተፉ የቆዩ አገሪቱ ክለቦች የመጀመሪያውን ዙር ካልሆነ ያሳኩት ታሪክ የለም፡፡ ደደቢትም የዚሁ ዕጣ ተጋሪ ሆኗል፡፡

ባለፈው እሑድ (መጋቢት 27 ቀን 2007 ዓ.ም.) በዓይነቱና በይዘቱ ልዩ በሆነው የባሕር ዳር ሁለገብ ስታዲየም የሁለተኛ ዙር ጨዋታውን ከናይጄሪያው ዋሪ ዎልቭስ ጋር ያደረገው ደደቢት ከሜዳው ውጪ የተቆጠሩበትን ሁለት ጐሎች ማካካስ የሚችል አቅም በማጣቱ  ከአሕጉራዊው መድረክ በጊዜ ለመሰናበት ግድ ብሎታል፡፡

ከወራት በፊት በዋና አሠልጣኝነት በተረከቡት ኢንስትራክተር ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው ደደቢት ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፈውን ውጤት ለማግኘት ማጥቃትን መሠረት አድርጐ ወደ ሜዳ ቢገባም፣ ኳስና መረብን ማገናኘት ባለመቻሉ የተሳትፎውን ዕድል ለእንግዳው ቡድን ዋሪ ዎልቭስ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ዋሪ ዎልቭስ ከሁለት ሳምንት በፊት በሜዳው ደደቢትን ሁለት ለዜሮ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ የተከታተሉ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎችና ተመልካቾች ሥጋት ግን የደደቢት ሽንፈት ብቻ ሳይሆን፣ የአገሪቱ እግር ኳስ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ጭምር መሆኑን ነው የሚያስረዱት፡፡

ከእነዚህ አስተያየት ሰጪዎች መካከል በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል የሦስተኛ ዓመት ተማሪ የሆነው መሳይ አለባቸው ይጠቀሳል፡፡ የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች ለዚህ ጨዋታ ወደ ባሕር ዳር ከመጡበት መጋቢት 22 ቀን ጀምሮ ያደረጉትን ዝግጅት ተከታትሏል፡፡ ከልምምድ በኋላም ከአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጋር ተገናኝቶ መሠረታዊ በሚባሉ የእግር ኳስ ሥልጠናዎች ዙሪያ አንዳንድ ጉዳዮችን በማንሳት እንደተነጋገረ የሚናገረው ተማሪ መሳይ ከውይይቱ የተረዳው የአገሪቱ እግር ኳስና የስፖርት ቤተሰቡ የሚመኙትን ውጤት ለማግኘት ፍላጎቱና ቁጭቱ ካላቸው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ ክልሎች፣ ክለቦችና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት መሬት ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ‹‹ምን እናድርግ?›› ብለው መነጋገርና ትክክለኛውን የለውጥ መንገድ መከተል እንደሚጠበቅባቸው ነው፡፡ ሌሎችም አስተያየት ሰጪዎች የደደቢትን ውጤት ተከትሎ የተናገሩት ሁሉም አካላት ያለፉበትንና ያልሠሩትን ለማግኘት ከሚያሳዩት የማስመሰል ቁጭትና ሪፖርት ወጥተው እግር ኳሱ የሚፈልገውን ትክክለኛውን አደረጃጀት በመፍጠር ለቦታው የሚሆኑትን ባለሙያዎች ማሰብ የግድ እንደሚላቸው ነው ያስረዱት፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...