Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየመንግሥት ልማት ድርጅቶችን በቦርድ የሚመሩ ኃላፊዎች ቁጥር በግማሽ እንዲቀንስ ተደረገ

የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን በቦርድ የሚመሩ ኃላፊዎች ቁጥር በግማሽ እንዲቀንስ ተደረገ

ቀን:

ከዚህ ቀደም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በቦርድ አመራርነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዴኤታዎችን ቁጥር በግማሽ እንደቀነሰ ይፋ ያደረገው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር፣ ነባር ሚኒስትሮችን ከቦርድ አመራርነት በማንሳት በምትካቸው ከትምህርት ተቋማትና ከሌሎች የሙያ መስኮች የተውጣጡ ባለሙያዎችን በቦርድ ማሳተፍ እንደጀመረ አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ሰሞኑን በጠራው ስብሰባ ወቅት በርካታ ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዴኤታዎች የተገኙ ሲሆን፣ የበርካታ ድርጅቶች አመራሮችም ተሳትፈዋል፡፡ በስብሰባው ወቅት በቀረበ ጥናት መሠረት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ ሊሆኑ ካልቻሉባቸው ምክንያቶች መካከል በቦርድ አመራርነት የሚሾሙ ኃላፊዎች ደካማ ሚና ተጠቅሷል፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ለጋዜጠኞች እንዳብራሩት፣ ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር መሠረት የቦርድ አመራሮችና አባላት ቢያንስ በየወሩ እየተገናኙ ስለሚመሯቸው ድርጅቶች በመነጋገር ለውጦች እንዲመገዘቡ ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ ይህንን የማያደርጉ በርካቶች እንደሆኑ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ከዚህ በተጨማሪ በአራት ድርጅቶች ውስጥ በቦርድ አመራር ድርሻ ያላቸው ነገር ግን ምንም ዓይነት ጊዜ የሌላቸው በርካታ ኃላፊዎች እንደነበሩ ዶ/ር ግርማ ጠቁመዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እንደማኛውም የንግድ ተቋም የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው፣ እነዚህ ተቋማት ውጤታማ ሆነው እንዲራመዱ ለማድረግ ሲባል ከዚህ በኋላ በአንድ ድርጅት ውስጥ ቢባዛ ከሁለት የማይበልጥ ሹመት ያላቸው ኃላፊዎች እንደሚመደቡ ያስታወቁት ሚኒስትሩ፣ በጠቅላላው ከነበራቸው ብዛትም በግማሽ እንዲቀንሱ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡ በመሆኑም ግማሹን ቁጥር የሚሸፍኑት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለሙያዎች፣ በልዩ ልዩ ሙያ የተሠማሩና የየድርጅቱ ሥራ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የሒሳብ አዋቂዎችና የመሳሰሉት እንደሚሆኑም አስረድተዋል፡፡

በዚህ መሠረት በተካሄደው ሽግሽግ ቀደምት የቦርድ ኃላፊዎች እንደተነሱ፣ በምትካቸውም አዳዲስ ኃላፊዎች እንደተተኩና ሌሎችም እንደሚቀላቀሏቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመሆኑም ሚኒስቴሩ በቀጥታ በሚቆጣጠራቸው 23 የልማት ድርጅቶች ውስጥ የቦርድ አባልም አመራርም በመሆን የሚሳተፉ የመንግሥት ተlሚዎች ቁጥር በግማሽ እንዲቀነስ ይደረጋል ማለት ነው፡፡

ይህንን ለማድረግ ማኬንዚና ኩባንያው በተባለ የአሜሪካ አማካሪ ድርጅት በኩል ጥናት ማስጠናቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ አብዛኞቹ የልማት ድርጅቶች በኪሳራ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን፣ በርካቶቹም በፋይናንስና በሌሎች ንብረቶች አያያዝ ከአቅም በታች በማምረት ሒደት ውስጥ ሲዳክሩ የኖሩ እንደነበሩ በጥናት መረጋገጡንና ለዚህ አስተዋጽኦ ያደረጉት ደግሞ ድርጅቶቹ ሲመሩባቸው የነበሩት አስተዳደራዊ መዋቅሮች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በሚያዝያ ወር መጀመሪያ በቦርድ አመራርነት ለተመደቡ አዲስና ነባር ኃላፊዎች የሁለት ሳምንት ሥልጠና ማዘጋጀቱን ሚኒስቴሩ ቢያስታውቅም፣ በዚህ አጭር ሥልጠና አማካይነት ያሰበውን ለውጥ ስለማምጣቱ ግን ጥርጣሬ እንደሚያጭር የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር ልማት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ውለታው ገልጸዋል፡፡ ‹‹ስንት የአመራር ክህሎት ያለን ሰዎች የቢዝነስ ተቋማት አመራር ክህሎትን ለማግኘት 45 ቀናት ከፈጀብን በሁለት ሳምንት ሥልጠና ምን ያህል ጥራት ያለው ውጤት ሊኖራችሁ ይችላል?›› በማለትም ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ሌሎችም ሚኒስትሮችና በተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ አባላትም ጥያቄዎቻቸውንና በአዲሱ ለውጥ ላይ ያላቸውን ሐሳብ አካፍለዋል፡፡

ከ23 ድርጅቶች መካከል ሦስቱ ብቻ ኪሳራ ማስዝገባቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ እንዚህም ኮስቲክ ሶዳ፣ የፐልፕና ወረቀት ድርጅት እንዲሁም የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ መንግሥት የኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካን ለማሻሻል 600 ሚሊዮን ብር በመመደብ አዲስ ግንባታ እንደሚያካሂድ፣ የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅም በቅርቡ ወደ ግል እንደሚዛወር ይፋ አድርገዋል፡፡

እስካሁን 300 የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ያዛወረው ተቋም፣ ከሌሎች ኩባንዎች ቀሪ ያልተከፈለ ሒሳብ እንዲከፈለው እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አዲሱ ሚኒስትር ሥራ በጀመሩ ማግሥት ውዝፍ ዕዳ ያለባቸውን ኩባንያዎች በመጥራት ማነጋገራቸውን፣ የዕዳ አከፋፈል ፕሮግራማቸውን የሚሳይ ዕቅድ እንዲያቀርቡ ከማድረጋቸውም ባሻገር አዲስ የዕዳ አከፋፈል ስምምነት እንዲፈርሙ በማድረግ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ ይፋ በተደረገው የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት መሠረት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የ1.2 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገባቸው ታውቋል፡፡ ይህ ትርፍ የዕቅዳቸውን 92 በመቶ መሳካት እንደሚያመለክትም ተጠቅሷል፡፡ ከዚህም በላይ የ20.7 ቢሊዮን ብር ሽያጭ ማከናወን እንደቻሉም የሚኒስቴሩ መረጃ   ይጠቁማል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...