Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትእግር ኳስ ፌዴሬሽን ‹‹በጭቃ›› የተሸፈነውን እሾህ ቢያጠራ?

  እግር ኳስ ፌዴሬሽን ‹‹በጭቃ›› የተሸፈነውን እሾህ ቢያጠራ?

  ቀን:

  የእግር ኳስ ቤተሰቡ እምብዛም በዝርዝር እንደማያውቀው የሚነገርለት የቴክኒክ ኮሚቴና ቴክኒክ ዲፓርትመንት ሚናና አደረጃጀት ለአገሪቱ እግር ኳስ ቁልፍ ከሚባሉት ኃይሎች አንዱና ዋናው ነው፡፡ ይህ የሙያ ዘርፍ አሠልጣኞችንና ተጫዋቾችን ከመገምገምና የቡድን ግንባታው ላይ እሴት ከመጨመር ጀምሮ በትልልቅ ውሳኔዎች ላይ ተሳታፊና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን አመንጪ ሊሆን እንደሚገባውም ይታመናል፡፡

  ይሁንና በፌዴሬሽኑ ይህንን ሥልጣንና ኃላፊነት የተጣለበት ተቋም እግር ኳሱን ጽንሰ ሐሳብ በጥልቀትና በዝርዝር ይረዳሉ ተብለው ሚታሰቡ የስፖርት ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች እንደሚያካትት ተደጋግሞ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ይህም በሌላው አገር ከተለመደውና እግር ኳስ ከሚከተለው አደረጃጀት አንፃር ሲታይ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አሠራር ክፍተቶች እንዳሉበት አመላካች ሆኗል፡፡

  ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ በይፋ ባይገለጽም በቅርቡ ከብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝነት እንደተነሱ እየተነገረላቸው የሚገኙት ፖርቱጋላዊው አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ፣ ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴውንና ቴክኒክ ዲፓርትመንቱን ካላግባቧቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ‹‹መናናቅ›› እና አለመተማመንን መሠረት ያደረገ ችግር እንደሆነም እየተነገረ ይገኛል፡፡ ይህንኑ መነሻ አድርገው የእግር ኳሱ ቤተሰቦች እንደሚናገሩት ከሆነ  የዚህን የቴክኒክ ኮሚቴና የቴክኒክ ዲፓርትመንት የአቅም ሁኔታ በመጠራጠር በኮሚቴው ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው ትክክለኞቹ የሚሏቸውን ባለሙያዎች ሊፈለጉና ኃላፊነቱም ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ እነዚህም የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋቾችና በስፖርቱ  የሠለጠኑትን እንዲሁም በእግር ኳስ ተንታኝነት ዓለም አቀፍ ዕውቅናን የተላበሱ ሊሆኑ እንደሚገባም ይናገራሉ፡፡

   ምክንያቱም የሚሉት እነዚሁ አካላት፣ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰሞኑን በአሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ ከአቅም ጋር የተያያዙ ችግሮች እንደገጠመው ሲነገር መሰንበቱ በይፋ መነገሩ ነው፡፡ ለዚህ እንደ መፍትሔ የሚቀርበው ደግሞ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ‹‹በጭቃ›› የተሸፈነውን እሾህ ሊያጠራ ይገባዋል የሚል ነው፡፡

  የአሠልጣኝ ማርያኖ ባሬቶን የሙያ ብቃትና ከዋልያዎቹ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ገምግሞ ለፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲያቀርብ ኃላፊነት የተጣለበት ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ ያቀረበው የቴክኒክ ግምገማ ብቁ ሆኖ ባለመገኘቱ ጉዳዩ በሌላ ኮሚቴ እንዲታይና ለውሳኔ እንዲቀርብ መወሰኑም ይታወቃል፡፡

  ይህም በብዙኃኑ የእግር ኳስ ቤተሰብ ዘንድ የእግር ኳሱ ቁልፍና ዋነኛ መሆኑ የሚነገርለት ‹‹በቴክኒክ ኮሚቴና በቴክኒክ ዲፓርትመንት ክፍል አማካይነት በርካታ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍና የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሲቀርፁ የቆዩት ባለሙያዎች ዛሬ በአሠልጣኝ ማሪያኖ ጉዳይ ያቀረቡት የግምገማ ሪፖርት ከሙያ ብቃት አኳያ ውድቅ ከሆነ እነዚህ ክፍሉን እንዲመሩ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው የቆዩት አካላት እስከ ዛሬ ለምን ቆዩ?›› የሚለው ፌዴሬሽኑን ለትችት እየዳረገው ይገኛል፡፡

  ለደኅንነታቸው ሲሉ ማንነታቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የፌዴሬሽን አንዳንድ ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ የሚጠበቅ ቢሆንም የፖርቱጋላዊው አሠልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ  ጉዳዩ ያበቃለት ነው፡፡ በውሳኔው ቅሬታ ባይሰማቸውም የአሠልጣኙ መባረር ብቻውን ለእግር ኳሱ መፍትሔ ሊሆን እንደማይችል ግን አልሸሸጉም፡፡

  እንደ ሙያተኞቹ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአሠልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ እኩል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ራሱንና በሥሩ ያዋቀራቸውን ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴና ቴክኒክ ዲፓርትመንት እንዲሁም በሌሎችም ንኡሳን ኮሚቴዎች አማካይነት እየተመሩ የሚገኙ ዲፓርትመንቶች (ክፍሎች) በምን ዓይነት ባለሙያዎችና አቅም ላይ እንደሚገኙ የመገምገምና የማጥራት ሥራ ሊሠራ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ የሚጠበቅባቸውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ መጠየቅ ያለባቸው እነዚህ ክፍሎችና ክለቦች ባደራጁላቸው መዋቅራዊ የአሠራር ሥርዓት በተገኙ ተጨዋቾች መሆኑ ከግምት ገብቶ ማየትና መመልከት እንደሚያስፈልግም ይመክራሉ፡፡

  ይህ ካልሆነ ግን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የቀድሞ አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻውን አሰናብቶ ከባሕር ማዶ ደረጃውን የጠበቀ አሠልጣኝ ያመጣበት መንገድ በቅጡ ሳያጤነውና ሳይገባው የመረጠው መንገድ መሆኑን የሚናገሩት እነዚሁ የፌዴሬሽን ባለሙያዎች፣ አሁንም ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› እንዳይሆን ውስጡን ሊያጠራ እንደሚገባው ጭምር ይጠቁማሉ፡፡ 

     

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...