Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን የህዳሴውን ግድብ የሚያጠና ድርጅት መረጡ

ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን የህዳሴውን ግድብ የሚያጠና ድርጅት መረጡ

ቀን:

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በአዲስ አበባ ባደረጉት የሁለት ቀናት ዝግ ስብሰባ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የተፅዕኖ ሥጋትን የሚያጠና ኩባንያ መምረጣቸውን አስታወቁ፡፡

ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረባቸው ሁለት ምክረ ሐሳቦች ለመተግበር በወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ከተለዩ አራት ድርጀቶች መካከል፣ አንድ የፈረንሳይና አንድ የኔዘርላንድ ኩባንያ ቀርተው ነበር፡፡ ከእነዚህ ኩባንያዎች አንዱን ለመለየት በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት የቆየ አድካሚ ስብሰባ ተካሂዶ በመጨረሻ ሚያዝያ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ተጠናቋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል እንዲመረጥ የሚፈለገው ድርጅት የፈረንሳዩ ቢአርኤል ኢንጂነርስ የተባለ ኩባንያ፣ በግብፅ በኩል ደግሞ የኔዘርላንዱ ዴልታሬዝ ኩባንያ እንዲመረጥ በመፈለጉ ምክንያት ስምምነት ላይ ለመድረስ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ኢትዮጵያ የመረጠችው ኩባንያ በኢትዮጵያ የተለያዩ የማማከር ሥራዎችን ያከናወነ ሲሆን፣ የኔዘርላንዱ ኩባንያም በግብፅ ተመሳሳይ ሥራ መሥራቱን ምንጮች ያስረዳሉ፡፡

እስካለፈው ሐሙስ ከሰዓት በኋላ ድረስ ኢትዮጵያና ሱዳን የፈረንሳዩን ኩባንያ በመምረጥ ግብፅን ለማሳመን ሲጥሩ ከቆዩ በኋላ፣ በሱዳን በኩል በቀረበ አማራጭ ሐሳብ ሊስማሙ መቻላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚሁም መሠረት የፈረንሳዩ ኩባንያ ዋናውን የማማከር ሥራ እንዲሠራ፣ የኔዘርላንዱ ኩባንያ ደግሞ ‹ሰብኮንትራት› ወይም የተወሰነ የማማከር ድርሻ እንዲኖረው ሐሳብ ቀርቦ በግብፅ በኩልም ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

እልህ አስጨራሽ የነበረው ስብሰባ እንደተጠናቀቀም በሦስቱም መንግሥታት የውኃ ሚኒስትሮች መግለጫ ቢሰጥም፣ የተመረጡት ኩባንያዎችን ስም ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡ የሰጡት ምክንያት ደግሞ በቅድሚያ የተመረጠው ኩባንያ ማወቅ ያለበት ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡

የተመረጠው የፈረንሳዩ ኩባንያ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውኃ የሚሞላበትንና የአለቃቅ ሞዴሉን (ኃይድሮ ሲሙሌሽን ሞዴል) እና ሊያደርስ የሚችለውን የአካባቢያዊና ማኅበራዊ ተፅዕኖ የሚገመግም ሲሆን፣ ሁለተኛው ኩባንያ ከዚህ ውስጥ የተወሰኑ ሥራዎችን ያገኛል፡፡ ይሁን እንጂ የሥራው ዓይነት አልታወቀም፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...