Sunday, May 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየጤፍ የባለቤትነት መብት ለማስከበር እየተሠራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ አስታወቁ

የጤፍ የባለቤትነት መብት ለማስከበር እየተሠራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ አስታወቁ

ቀን:

በዓለም ገበያ ከፍተኛ ተፈላጊነትን እያገኘ ያለውን የጤፍ ምርት የዘር ባለቤትነትን ለማስከበር መንግሥት እየሠራ መሆኑን፣ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት፣ ከምክር ቤቱ አንዳንድ አባላት የጤፍ ዘርና ምርት ከኢትዮጵያ ውጭ በተለያዩ አገሮች የሚገኝ መሆኑን በመጥቀስ የግብርና ሚኒስቴር የዚህ የእህል ዘር ባለቤት ኢትዮጵያ ብቻ መሆኗን በሕግ ከማረጋገጥ አኳያ ምን እየሠራ እንደሆነ እንዲያብራሩ ጠይቀዋል፡፡ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ ኢትዮጵያ የጤፍ ዘር ባለቤት መሆኗን ለማስከበር፣ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑንና ይህንን ጉዳይ የሚከታተል አንድ ግብረ ኃይል መቋቋሙንም ተናግረዋል፡፡ ‹‹በዋነኝነት ግን እሴት መጨመርና በዓለም ገበያ ውስጥ በስፋት መግባት ትኩረት ተሰጥቶታል፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹በአሁኑ ወቅት ጤፍ የማያመርት አገር አለ ማለት ይከብዳል፤›› በማለት በበርካታ የዓለም አገሮች በእጅጉ ተፈላጊ ምርት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የጤፍ ምርት ግሎቲን ከተባለው የፕሮቲን ዓይነት ነፃና ለጤና ተስማሚ በመሆኑ፣ በከፍተኛ ደረጃ በዓለም አገሮች ተፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በተለይም የግሎቲን አለርጂክ በሆኑ የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ አገሮች በእጅጉ ተፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ አገሮች ጤፍን በማምረት ላይ ቢሆኑም፣ ለኢትዮጵያ የባለቤትነት ክፍያ እየከፈሉ አይደሉም፡፡ ቢሆንም መሠረታዊ ይዘቱ ከኢትዮጵያ ጋር የሚወዳደር ባለመሆኑ ይህንኑ የኢትዮጵያ ጤፍ ልዩ ባህሪ በመያዝ ወደ ገበያ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡ የጤፍ ዘርን ወደ ውጭ አገር መላክ የተከለከለ በመሆኑ፣ በርካታ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች የጤፍ ምርት የሆኑ ምግቦችን ወደ አውሮፓና አሜሪካ በመላክ ላይ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህል አንድ ኩባንያ ብቻ በየቀኑ ሦስት ሺሕ እንጀራ ወደ አሜሪካ እየላከ መሆኑን ቢቢሲ ሰሞኑን ዘግቧል፡፡ በተመሳሳይም በሳምንት ሦስት ጊዜ ወደ ስዊዲን፣ በሳምንት ሁለቴ፣ ወደ ኖርዌይ ወደ ጀርመን ደግሞ በሳምንት ሦስት ጊዜ እየተላከ ይገኛል፡፡ ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ለፓርላማው እንደገለጹት፣ ከ20 ሔክታር በላይ የጤፍ ማሳ ያላቸው ባለሀብቶች ጤፍን በዱቄት መልክ ወይም እሴት ጨምረው እንዲልኩ ከመጪው ዓመት ጀምሮ መንግሥት ሰፊ ሥራ ይሠራል፡፡ ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው የአገሪቱን ሰብል ልማት ውጤት ይፋ ያደረጉ ሲሆን፣ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ የተጣለውን ግብ ሙሉ በሙሉ ማሳካት ባይቻልም ከ90 በመቶ በላይ የግብርና ሰብል ልማት ዕቅድን ማሳካት እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ በቡና ልማት በምርት ዘመኑ ምርት ከሚሰጥ 815 ሺሕ ሔክታር የቡና ማሳ ላይ 831 ሺሕ ቶን ቡና ለማምረት፣ ምርታማነትን በአማካይ በ10.2 ኩንታል በሔክታር ለማድረስ ታቅዶ በተደረገው የቅድመ ምርት ዳሰሳ፣ ምርት መስጠት ከሚችለው 778,672 ሔክታር የቡና ማሳ 548,185 ቶን ቡና እንደሚመረት መገመቱን አስረድተዋል፡፡ የሆርቲካልቸር ልማትና ኤክስፖርትን ከማጠናከር አኳያ በ2007 ዓ.ም. ዘጠኝ ወራት 230.49 ሚሊዮን ዶላር እንደሚገኝ ታቅዶ፣ 158.5 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ የፓርላማው የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚኒስቴሩን የሥራ አፈጻጸም አድንቆ በእንስሳት ሀብት ልማት፣ በግብርና ኤክስፖርት አፈጻጸም፣ በዘመናዊ የግብርና መሣሪያዎችና ግብዓቶች የታዩ ድክመቶች እንዲስተካከሉ መመርያ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...