Friday, July 12, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያን በውጤታማ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ ሥራ ሸለመ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ‹የተባበሩት መንግሥታት የ2017 ሽልማት›ን በትኩረታዊ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ፣ ማስተባበርና ዘላቂነት ባለው ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ተሸለመ፡፡

ኮሚሽኑ ሽልማቱን ያገኘው ትናንት ኅዳር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. በስዊዘርላንድ በተካሄደው በተባበሩት መንግሥታት የንግድና የልማት ኮንፈረንስ ዘጠነኛ የኢንቨስትመንት፣ ኢንተርፕራይዝና ልማት ኮሚሽን ላይ ነበር፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽኑ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ ‹‹በተለይ የኢትዮጵያ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ባህርያት፣ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ታዋቂ ኢንቨስተሮች እንዲገቡ ያስቻለ ትኩረታዊ የኢንቨስተሮች አመራረጥና ኢንቨስተሮቹ የተደረገላቸው ማፋጠን የሚመሰገንና ለሌሎች አገሮች ምሳሌ ሊሆን የሚችል ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትከተለው ፖሊሲ ብዙ ሰውን መቅጠር የሚያስችሉ እንደ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ያሉት ዘርፎች በርካት ወጣቶችን ወደ ሥራ የሚያስገቡና  ለሴቶች እኩል ዕድልን የሚሰጡ ኢንዱስትሪዎችን የማስፋፋት፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ላይ የሚታየው ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊና አካባቢያዊ ደረጃዎችን የማሟላት ሂደትና አገሪቱ ስትራቴጂክ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ለኢንቨስተሮች ተስማሚ የሆኑ ማሻሻያዎችን ማድረጓ ይህንን ሽልማት እንድታገኝ አድርገዋታል፤›› ብሏል፡፡

በሽልማቱ ላይ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍጹም አረጋ የተመራ የልዑካን ቡድን ሽልማቱን የተቀበለ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት አምባሳደር አቶ ነጋሽ ክብረት በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተግኝተው ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች