Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊዕጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ ቤቶች ግንባታ አለመጠናቀቁና የውኃ ችግር ሊፈታ አለመቻሉ ተገለጸ

ዕጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ ቤቶች ግንባታ አለመጠናቀቁና የውኃ ችግር ሊፈታ አለመቻሉ ተገለጸ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ከአምስት ዓመታት የግንባታ ጊዜ ቆይታ በኋላ በ2009 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ በዕጣ ካስተላለፋቸው የ40/60 የጋራ መኖርያ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ውስጥ፣ በክራውን የሚገኙ ሕንፃዎች ግንባታ ሊጠናቀቅ አለመቻሉና የውኃ ቆጣሪ ሊገባ እንዳልቻለ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ባደረገው ጥናት፣ በዕጣ ከተላለፉ የ40/60 የጋራ መኖርያ ቤቶች መስተካከል ያለባቸውና የማጠናቀቂያ ሥራ እንደሚቀር አረጋግጧል፡፡

የጋራ መኖርያ ቤቶቹ ከአምስት ወራት በፊት መቶ በመቶ ለከፈሉ ሰዎች በዕጣ የተላለፉ ቢሆንም፣ የሚቀራቸው ግንባታ ስለነበር እስካሁን ነዋሪዎቹ ሊገቡ አለመቻላቸውን ባለንብረቶቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የጋራ መኖርያ ቤቶቹ ዕድለኛ ከሆኑት ውስጥ አቶ ፀጋው ብርሃኑ፣ አቶ ይገረም ደምስ፣ ወ/ሮ ላቀች ሰለሞንና አቶ ፍጹም አብርሃ ይገኙበታል፡፡ ዕድለኞቹ እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤቶቹን በዕጣ ሲያስተላልፍላቸው ደስታም ቅሬታም ተሰምቷቸዋል፡፡ ዕጣው ስለደረሳቸው ደስታ ቢሰማቸውም፣ መቶ በመቶ ክፍያ ከፈጸሙ ከአምስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ከ365,000 ብር በላይ ከነወለዱ እንዲከፍሉ መደረጋቸው ደግሞ ቅር እንዳሰኛቸው አስረድተዋል፡፡ ወ/ሮ ላቀች አክለው እንደተናገሩት፣ ሲመዘገቡ ከከፈሉት የገንዘብ መጠን የሚስተካከል ተጨማሪ ክፍያ ሲከፍሉ የተለያዩ ነገሮችን ማለትም የግንባታ ዕቃዎች፣ የሠራተኛ ጉልበትና ሌሎች ወጪዎችን ታሳቢ በማድረግ ክፍያውን ፈጽመዋል፡፡ የሚገርመውና የሚያናድደው ድርጊት ቤቱን ወዲያው እንደሚረከቡ ተነግሯቸው እስካሁን ግንባታው አለመጠናቀቁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ንግድ ባንክን ሲጠይቁ ወደ ኢንተርፕራይዙ እንደሚመራቸው፣ በኢንተርፕራይዙ ደግሞ የሚያነጋግራቸው አለማግኘታቸውን ገልጸው በመሀል ቤት ለተጨማሪ የቤት ኪራይ ወጪ መዳረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ባይጠናቀቅ እንኳን ካለባቸው ችግር አንፃር ዝም ብለው እንዳይገቡ የውኃ መስመር እንጂ የውኃ ቆጣሪ እንዳልገባላቸው፣ የኤሌክትሪክ ኃይልም እንዳልተለቀቀ አስረድተዋል፡፡ የወቅቱን የቤት ኪራይ መንግሥትም ሆነ በሥልጣን ላይ ያሉ ሁሉ ስለሚያውቁት፣ ችግራቸውን ተመልክተው መፍትሔ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል፡፡

ሪፖርተር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊዎችን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ባቀረበው ጥናታዊ ሪፖርት እንዳረጋገጠው፣ በተላለፉ የ40/60 መኖርያ ቤቶች መስተካከል ያለባቸው የማጠናቀቂያ ሥራዎች ይቀራሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አቃቂ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ታፈሰ በሰጡት ምላሽ እንደገለጹት፣ ከ40/60 ባለዕድለኞች ጋር ውል እየተዋዋሉ ነው፡፡ የቆጣሪ ችግር ቢኖርባቸውም ለልማት ተነሺዎችና የኮንደሚኒየም ቤቶች ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡ ከ1,000 በላይ ቆጣሪዎች አሏቸው፡፡ እነሱ ከ400 ስለማይበልጡ በሚቀጥለው ሳምንት ሙሉ በሙሉ እንደሚገጥሙ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሰለሞን እንደ ችግር ያነሱት የውኃ ቆጣሪ ቢገጠምም፣ በሕንፃው ሥር መገጠም የነበረበት ፓምፕ ስላልተገጠመ ውኃውን ማሰራጨት ወይም መግፋት እንደማይቻል ነው፡፡ ይህ ደግሞ የኢንተርፕራይዙ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን በሚመለከት፣ የአገር አቀፍ ኮንዶሚኒየም ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋይ ንርአዮ ሙሉ በሙሉ ተዘርግቶና ኃይልም ተለቆ መጠናቀቁን ገልጸው፣ በኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል ምንም ችግር እንደሌለ አረጋግጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...