Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ የድርቅ ተጋላጭነትን የሚቃኝ ቡድን ተንቀሳቀሰ

በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ የድርቅ ተጋላጭነትን የሚቃኝ ቡድን ተንቀሳቀሰ

ቀን:

  • የተረጂዎች ቁጥር ከ8.5 ሚሊዮን ሊቀንስ ይችላል
  • ከኦሮሚያና ከሶማሌ የተፈናቀሉ ዜጎች ለማቋቋም የሰላም ኮንፈረንስ ይጠበቃል

እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 1 ቀን 2018 በኋላ በድርቅ ምክንያት የሚኖረው የተረጂዎች ቁጥር ለማወቅና የሚያስፈልገውን በጀት ከወዲሁ ለመመደብ፣ የመጨረሻውን ቅኝት የሚያካሂድ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ተንቀሳቀሰ፡፡

ቅዳሜ ኅዳር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የተንቀሳቀሰው የባለሙያዎች ቡድን በኦሮሚያ ክልል ቦረና ለ21 ቀናት፣ በሶማሌ ክልል ደግሞ ለ25 ቀናት ቅኝት አድርጎ ይመለሳል ተብሏል፡፡

ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ዝናብ የሚጥለው በመስከረምና በጥቅምት ወር ነው፡፡

‹‹በቦረና የሚጥለው ዝናብ አገያ ይባላል፡፡ በሶማሌ ክልል ጥቅምት ወር የሚጥለው ዝናብ ደአር ይባላል፡፡ የዝናቡ ሁኔታ የተረጂዎችን ቁጥር ይወስናል፤›› ሲሉ አቶ ምትኩ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የጣለው ዝናብ አጥጋቢ ከሆነ ድርቅ ይቀንሳል፣ አጥጋቢ ካልሆነ ደግሞ ድርቅ ይኖራል፤›› ብለዋል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ በአካባቢው ዝናብ ጥሏል፡፡ ነገር ግን በአንዳንድ ኪስ ቦታዎች አነስተኛ የዝናብ መጠን መጣሉ ታውቋል፡፡

በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው ተከታታይ ድርቅ 8.5 ሚሊዮን ዜጎች የምግብ ዋስትና ችግር ተከስቶባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ አቶ ምትኩ በጥር ወር ይፋ ሲደረግ የተረጂዎች ቁጥር ይቀንሳል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡

ምክንያቸውን ሲያስረዱም በደጋና በወይና ደጋ አካባቢዎች አጥጋቢ ዝናብ በመዝነቡ፣ እንዲሁም አርብቶ አደር አካባቢዎች በተለይም በሶማሌ ክልል የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውኃ ሀብቶች በመልማታቸው፣ አሁንም የተረጂዎች ቁጥር የሚቀንስ መሆኑ ለዚህ ድምዳሜ እንዳደረሳቸው አብራርተዋል፡፡

‹‹የደቡብ ምሥራቅ የአገሪቱ ክፍል ሁኔታ እየታየ በመሆኑ አሁን ላይ መናገር ባይቻልም፣ ከአጠቃላይ ግምገማ በመነሳት ግን የተረጂዎች ቁጥር ከ8.5 ሚሊዮን የመቀነስ እንጂ የመጨመር አዝማሚያ አያሳይም፤›› ሲሉ አቶ ምትኩ ገልጸዋል፡፡

የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከተፈጥሯዊ አደጋ በተጨማሪ ለሰው ሠራሽ አደጋዎችም ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ፣ ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልሎች ለተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አቶ ምትኩ አስረድተዋል፡፡

‹‹የተፈናቀሉ ዜጎችን በቋሚነት ለማቋቋም የልማትና የሰላም ኮንፈረንስ መካሄዱን እየጠበቅን ነው፤›› ሲሉ ገልጸው፣ ‹‹የሰላም ኮንፈረንሱ ከተካሄደ በኋላ ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት በመመለስ በቋሚነት የማቋቋም ሥራ ይጀመራል፤›› ብለዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...