Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናክስ የተመሠረተባቸው የወልቃይት ሕዝብ ማንነት አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በዳኛ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ክስ የተመሠረተባቸው የወልቃይት ሕዝብ ማንነት አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በዳኛ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ቀን:

  • ፍርድ ቤቱ ተቃውሞአቸውን በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል

በሽብር ተግባር ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ወይም ፍትሕ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ ሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ለማየት ከተሰየሙት ሦስት ዳኞች መካከል በአንደኛው ዳኛ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰሙ፡፡

በዕለቱ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ከተሰየሙት ዳኞች መካከል አቶ ዘርዓይ ወልደ ሰንበት የተባሉት ዳኛ፣ ጉዳያቸውን መመልከት እንደማይችሉ ተከሳሾቹ ለችሎቱ ገልጸዋል፡፡

በዳኛው ላይ ተቃውሞአቸውን ያቀረቡት ተከሳሾች አቶ መብራቱ ጌታሁን፣ አቶ አታላይ ዛፌ፣ አቶ አለነ ሻማ፣ አቶ ጌታቸው አደመና አቶ ነጋ ባንቲሁን የሚባሉ ሲሆኑ፣ የተቃውሞ ነጥባቸውንም አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

እንደ ተከሳሾቹ ገለጻ፣ ዳኛ ዘርዓይ እነሱን ለክስ ባበቃቸው የወልቃይት ሕዝብ ማንነት ጥያቄ ላይ አቋም ይዘው ‹‹የወልቃይት የማንነት ጥያቄ በታሪክና በሕገ መንግሥቱ›› በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ በድረ ገጽ ላይ አስፍረዋል፣ በቴሌቪዥንም ሐሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ በመሆኑም ዳኛው የእነሱን የክስ ሒደት በሚመረምሩበትና ውሳኔ በሚሰጡበት ሒደት ውስጥ የጥቅም ግጭት ስላለ በነፃነት ውሳኔ ይሰጣሉ ብለው ስለማያምኑ ጉዳያቸውን ማየት እንደሌለባቸው በመግለጽ ተቃውሞአቸውን አቅርበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በዕለቱ ተከሳሾችን ቀጥሮ የነበረው ቀደም ብለው በነበሩት ችሎቶች (በ2009 ዓ.ም.) በተከሳሾቹ ላይ የዓቃቤ ሕግን ምስክሮች ተቃውሞ ከቀረበባቸው ዳኛ በስተቀር ሌሎች ዳኞች ምስክሮቹን ሰምተው በመጨረሳቸው ብይን ለመስጠት ነበር፡፡ ተቃውሞ የቀረበባቸው ዳኛ ባይሰየሙም ብይኑ አለመድረሱ ታውቋል፡፡ በመሆኑም ችሎቱ እንደገለጸው፣ በዳኛው ላይ በቃል የተናገሩትን ተቃውሞ ሐሙስ ኅዳር 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ሌሎች በተመሳሳይ ክስ የተመሠረተባቸውም እነ ክንዱ ዱቤ (አሥር ተከሳሾች)፣ እነ ብርሃኑ ሙሉ (አራት ተከሳሾች) እና አቶ ጌታሁንም ተመሳሳይ ተቃውሞ በማቅረባቸው፣ እነሱም ለኅዳር 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ተቃውሞአቸውን በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ ምስክር ባሰማባቸው ተከሳሾች ላይ ብይን የሚሰጠውና የቀሪዎቹንም ክስ መመርመር የሚጀመረው በዳኛው ላይ የቀረበው ተቃውሞ ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ መሆኑ ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል በሰሜን ጎንደር የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል በማለት በቁጥጥር ሥር በዋሉት እነ አቶ መብራቱ ጌታሁን (አምስት ተከሳሾች) ላይ፣ ዓቃቤ ሕግ አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 6)ን ተላልፈዋል በማለት የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ መመሥረቱ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...