Wednesday, September 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልአዲሱ የቡና ሙዚየም በቦንጋ

  አዲሱ የቡና ሙዚየም በቦንጋ

  ቀን:

  ኢትዮጵያ ሦስተኛውን ሺሕ ዓመት (ሚሌኒየም) በ2001 ዓ.ም. ለመቀበል በምትጣደፍበት ጊዜ ለክብረ በዓሉ መታሰቢያ እንዲሆን ከተወጠኑት መካከል አንዱ የቡና ሙዚየም መገንባት ነበር፡፡

  በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ የቡና ተክል በተገኘባት ካፋ መዲና ቦንጋ ሰኔ 21 ቀን 1999 ዓ.ም. የቡና ሙዚየም ለመገንባት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የተጣለው የመሠረት ድንጋይ እውን ሆኖ ከሰባት ዓመት በኋላ ለመመረቅ በቅቷል፡፡

  በ2,826 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሆነበት ሙዚየም፣ በካፋ ዞን የሚገኙ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች ተቀምጠውበታል፡፡

  በኢትዮጵያ ከቡና ጋር ተያይዞ የሚነሱ እሴቶችንና የቡናን ብዝሃ ሕይወት የሚወክሉ ስብስቦችንም አካትቷል፡፡

  የጫካ ቡና፣ ጥቅጥቅ ደን፣ ፏፏቴዎች ኅብር ፈጥረው በሚኖሩበት አካባቢ ላይ የሰፈረው የቦንጋው የቡና ሙዚየም ሕንፃ፣ ባህላዊውን የቤት አሠራር ከዘመናዊ ግብዓቶች ጋር ያዋደደ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡

  ጎጀብ ወንዝን መዳረሻው አድርጎ የተመሠረተው የካፋ ዞን በጫካ ቡና፣ በአገር በቀል ዛፎችና በተለያዩ ዕፀዋት የተሞላው ጥቅጥቅ ደኑ፣ በዩኔስኮ የክብር መዝገብ ውስጥ የሰፈረ ነው፡፡

  የማኅበረሰቡ የቤት አሠራር፣ የአለባበስ ልማድ፣ በአካባቢው ያሉ ተፈጥሯዊ ሀብቶች፣ የአመጋገብ ሥርዓት፣ የጦር፣ የእርሻና የቤት አገልግሎት ላይ የሚውሉ መሣሪያዎች በአዲሱ ሙዚየም ግብዓት እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

  ብሔራዊ ቡና ሙዚየምና ጥቅጥቅ ደኑ የቱሪስቶች መዳረሻ እንዲሆኑ የተጠናከረ ሥራ መሠራት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሙዚየሙን ሚያዝያ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ሲመርቁ ተናግረዋል፡፡

  በግንቦት 2005 ዓ.ም. የዓለም ሙዚየም ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በቦንጋ ሲከበር እንደተወሳውና በስፍራው የተገኘው ሪፖርተር እንደዘገበው፣ በወቅቱ ከባለሀብቱ ሼህ መሐመድ አሊ አላሙዲን የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተችሮት ነበር፡፡

  ከሰባት ዓመት በፊት የቡና ሙዚየም ጽንሰ ሐሳብ ያፈለቁት በወቅቱ የብሔራዊ ሚሌኒየም ጽሕፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ምርምርና ጥናት ተቋም ሙዚየም ኃላፊ ዶ/ር ሐሰን ሰዒድ ናቸው፡፡

  ዶ/ር ሐሰን፣ በአገራዊ ፋይዳው ላይ የነበራቸው ግልፅ አቋም ለስኬቱ ጥሩ መሠረት እንደሚጥል፣ የሙዚየሙ ዋና ግብም የአካባቢውን ስም ከማስጠራት ባለፈ ለአገሪቱ አንጡራ ሀብት የተሻለ የዕውቅ መድረክ መፍጠር መሆኑንም ተናግረው ነበር፡፡ 

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ጦርነቱና ውስጣዊ ችግሮች

  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው...

  መኖሪያ ሸጦ መዞሪያ!

  እነሆ ከመካኒሳ ወደ ጀሞ ልንጓዝ ነው። ቀና ሲሉት እየጎበጠ...

  በምግብ ራሳችንን የመቻል ፈተና

  በጋሹ ሃብቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ በምግብ ራሳችንን መቻል እጅግ በጣም የተወሳሰበ...