Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የሽልማቱ ድባብ

ትኩስ ፅሁፎች

ስምንተኛው አገር አቀፍ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሽልማት ኅዳር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሲካሄድ፣ በክብር እንግዳነት ተገኝተው የሸለሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባሰሙት ዲስኩር፣ ‹‹በአገሬ ፖለቲካ በቆየሁባቸው ሁለት አሠርታት የበርካታ ሽልማት ፕሮግራሞች ታዳሚ፣ ሸላሚም ሆኜ አውቃለሁ፡፡ ሁሉም መልካምና አንዳች ታላቅ ሥራ ለሠሩ የአገሬ ኢትዮጵያ ልጆች ዕውቅና የሚሰጥባቸው መድረኮች በመሆናቸው ኩራት ይሰማኛል፤›› ብለዋል፡፡

***

ነብርን ከጉድጓድ የማውጣት ጥረትን የሚያሳየው ፎቶ አሸናፊ ሆነ

አናንድ ቦራ የተባለው ህንዳዊ ማሀራሽትራ በተባለው የህንድ ግዛት ውስጥ በሚገኝ አንድ ጉድጓድ ውስጥ ‹‹ነብር ገብቷል›› የሚል የስልክ መልዕክት የደረሰው ከዛሬ አምስት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ ፎቶ አንሺው አናንድ ሲበር ነበር ከቦታው የደረሰው፡፡ እንደደረሰ ሦስት ሰዓታት የፈጀውን ነብሩን ከገባበት ጉድጓድ የማውጣት ትግል በካሜራው ማስቀረት ችሏል፡፡ ባልተጠበቀ አጋጣሚ ያነሳው ይህ ፎቶግራፍ ከአምስት ዓመታት በኋላ ባለፈው ሳምንት በህንድ ተካሂዶ በነበረ የፎቶግራፍ ውድድር አሸናፊ አድርጎታል፡፡ ሰዎች ነብሩን ለማዳን የሚያደርጉትን ጥረትና የነብሩን የጥርጣሬ ገጽታ የሚያሳው ይህንን ፎቶግራፍ አስመልክቶ አናንድ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር፡፡ ነብርን ከጉድጓድ የማውጣት ጥረትን የሚያሳየው ፎቶ አሸናፊ ሆነ    

 

 

‹‹ዝናብ ታቆማለህ ዝናብ ታዘንባለህ››

ወጣቱ ባለቅኔ ኤፍሬም ሥዩም ተሰማ ከቀደምት የኢትዮጵያ ነገሥታት እና ሊቃውንት የተወጣጡትን የግእዝ ቅኔያት አዛምዶና አፍታቶ አንድም እያለ የተረጐመበት መጽሐፉን በ2006 ዓ.ም. ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ ‹‹ተዋነይ ብሉይ የግዕዝ ቅኔያት ፍልስፍና›› በማለት በሰየመው መጽሐፉ ፵፱ኛው (49ነኛው) ደጃፍ፣ የሊቀ አእላፍ ልብሰ ወርቅ አየለ ዘደብረ መዊእ ባለ ሁለት መስመር (ስንኝ) ዕዝል ጉባኤ ቃና ‹‹ጽድቅ ውእቱ አውርዶ ወአቅሞ ዝናም በዕፅ

 በተኪለ ዕፀው ይመልዕ አኮኑ ዘዝናመ ሰማይ ሕፀፅ፡፡››

እንዲህ አፍታትቶ ተርጕሞታል፡፡

አንደኛው፣

‹‹በዕፅ ተጠቅሜ

እንጨት በጄ ይዤ

ዝናም አወርዳለሁ››

ዝናም አቆማለሁ አለና ነገረው፡፡

ሁለተኛው፣

ሐሰት ነው አልልም

ዝናብ ታቆማለህ

ዝናብ ታዘንባለህ

ዕፀዋትን ይዘህ ጥበብህ እውነት ነው፡፡

ምክንያቱም

ጥንትም ቢሆን ሰማይ ዝናብ የሚሰጠው

ከመሬት መዳፍ ላይ እንጨት ሲያይ ብቻ ነው፡፡

* * *

ፀጉራሙ ባለ መንጃ ፈቃድ

      ወጣቱ የመንጃ ፈቃድ ስላወጣ መኪናቸውን መጠቀም ይችል እንደሆነ ካህን አባቱን ጠየቃቸው፡፡ “አባቱም የትምህርት ውጤትህን ካሻሻልህ፣ መጽሐፍ ቅዱስህን ካጠናህ ፀጉርህን ከተስተካከልክ በጉዳዩ ላይ ልንገጋገር እንችላለን” አሉት፡፡

      ልጅየው ከወር በኋላ ነገሮችን አስተካክሎ መኪናቸውን መጠቀም ይችል እንደሆነ በድጋሚ ጠያቃቸው፡፡

      ውጤትህ ተሻሽሏል መጽሐፍ ቅዱስህንም በትጋት አጥንተሃል፡፡ ሆኖም ፀጉርህን አልተቆረጥክም አሉት፡፡

‹‹አባዬ፣ ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ሳስብ ነበረ፡፡ የሳምሶን ፀጉር ረጅም አልነበረምን? ሙሴና ኖህ እንዲሁም ኢየሱስ ረጅም ፀጉር አይደል የነበራቸው?››

‹‹እዚህ ላይ እውነት አለህ፣ ልጄ አሉ አባቱ ‹‹ነገር ግን እነዚህ የጠቀስካቸው ሁሉ የሚጓዙት በእግራቸው ነበር፡፡››
                         – አረፋዓይኔ ሐጐስ ‹‹የስኮትላንዳውያን ቀልዶች›› (2005)

* * *

ኧረ የልጁ ነገር ከምን ደረሰ?

አንዲት እናት ልጅዋ በእኩለ ሌሊት ነቅቶ እያለቀሰ ስላስቸገራት ‹‹ዝም በል አንተ ለቅሶህንም አላቆም ካልህ አውጥቼ ለጅብ ነው የምሰጥህ፡፡ ና ብላው አያ ጅቦ›› ስትል ልጁ ፈርቶ ዝም አለ፡፡ ነገር ግን ለካስ አንድ ጅብ በጓሮ በኩል ደፍጦ ሲያዳምጥ ካሁን አሁን አውጥተው ይጥሉታል  ብሎ በመጠበቅ ላይ ነበርና በር ተንኳኳ፡፡ ‹‹ማነህ?›› ሲባል፣ ‹‹ኧረ የልጁ ጉዳይ ከምን ደረሰ?›› አለ ይባላል፡፡

  • መክብብ አጥናው ‹‹ሁለገብ የአዕምሮ ማዝናኛ›› (2005)

* * *

በሩ ግን አልተዘጋም

በአንድ መንደር ውስጥ አግብታ ብዙም ሳትቆይ ባሏን በሞት የተነጠቀች አንዲት ሴት ትኖር ነበር፡፡ አጠገቧ ዓይኗን የምታሳርፍባትና የምታጽናናት ብቸኛ ልጅ ነበረቻት፡፡ አንድ ልጇንም በርኅራኄና በፍቅር አሳደገቻት፡፡ ይሁን እንጂ በጥንቃቄ ብታሳድጋትም ልጇ ካደገች በኋላ የበለጠ ወደ ዓለም አዘነበለችና መንደሯን ለቅቃ ወደ ዋናው ከተማ ጥላት ኮበለለች፡፡ የልጅቷ እናት በሐዘን ተሰብራ ልጄ ከዛሬ ነገ ትመለስ ይሆናል ብላ ብትጠብቃትም እሷን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፡፡

የኮበለለችው ልጇ እንድትመለስ ሌትና ቀን እየጸለየች ዓመታት አለፉ፡፡ አንድ ምሽት አንድ የእግር ዱካ ድምፅ ወደ ቤቷ በሚወስደው ጠባብ መተላለፊያ እየተቃረበ ሲመጣና ወደ በሩም ተጠግቶ የበሩን እጀታ እየፈራ እየተባ ሲነካ ሰማች፣ እጀታውም ድምፅ አሰማ፡፡ በእንቅልፍ ሰመመን እንዳለች አንድ ሰው ወደ ውስጥ መዝለቁን እናት ትሰማና ካልጋዋ ተፈናጥራ በመነሳት ወደ በሩ ታመራለች፡፡ የኮበለለችው ልጇ ናት፡፡ ልቧ በደስታ እየዘለለ ልጇን በፍቅር በእቅፏ ውስጥ ወሸቀቻት፡፡ እንደተቃቀፉም፣ ልጇ፣ ‹‹እማዬ፣ በዚህ በእኩለ ሌሊት ለምን በሩን አልቆለፍሺውም?›› ብትላት፣ እናት የልጇን ጸጉር እየደባበሰች፣

‹‹ልጄ ሆይ፣ አንቺ ከኮበለልሽበት ቀን ጀምሮ ምናልባት አንድ ቀን ስትመለሺ ልትቀበልሽ ሁሌ ዝግጁ የሆነች እናት እንዳለሽ እንድታውቂና ሳታመነቺ እንድትገቢ በማሰብ በሩ በቀንም ሆነ በሌሊት ተቆልፎ አያውቅም›› ስትል መለሰችላት፡፡

  • ኃይሌ ከበደ ‹‹ምስካይ›› (2004)

 

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች