Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኒዮ ሊበራል አራማጆች በመንደር ማሰባሰብ ተግባር ላይ ተፅዕኖ መፍጠራቸውን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር...

የኒዮ ሊበራል አራማጆች በመንደር ማሰባሰብ ተግባር ላይ ተፅዕኖ መፍጠራቸውን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር አስታወቁ

ቀን:

 በአገር ውስጥም በውጭም የሚገኙ የኒዮ ሊበራል ርዕዮተ ዓለም አራማጆች የመንግሥት የመንደር ማሰባሰብ ፕሮግራም እንዳይካሳ ተፅዕኖ እየፈጠሩ መሆኑን፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ገለጹ፡፡

 ሚኒስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም የሚኒስቴሩን የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት፣ በስምንት ወራት ውስጥ ሚኒስቴሩ ገጥመውታል ካሏቸው ዋና ዋና ችግሮች መካከል የኒዮ ሊበራሊዝም አራማጆች የመንደር ማሰባሰቡ ተግባር እንዳይሳካ ተፅዕኖ መፍጠራቸው ይገኝበታል፡፡

      መንግሥት የሕዝቡን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለያዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች የመንደር ማሰባሰብ ሥራ በመሥራት ዜጎች የትምህርት፣ የጤናና የመጠጥ ውኃ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  በአራቱ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች የመንደር ማሰባሰብ ተግባር መከናወኑን፣ በዚህም በሶማሌ ክልል 77,762፣ በአፋር ክልል 4,562፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 65,360 እንዲሁም በጋምቤላ ክልል 535 ነዋሪዎችን በአጠቃላይ 148,219 በመንደር በማሰባሰብ በግብርና ልማት፣ በመሬት ይዞታ ባለቤትነትና በትምህርት ተደራሽነት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በ2007 ዓ.ም. በእዚሁ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች 73,000 አባወራዎችንና እማወራዎችን በመንደር ለማሰባሰብ ታቅዶ በስምንት ወራት ውስጥ በድምሩ 13,000 አባወራዎች መሰባሰባቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህ አፈጻጸም ዝቅተኛ ቢሆንም በቀጣይ ወራት ማስተካከል እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ የኒዮ ሊበራል ርዕዮተ ዓለም አራማጆች አመለካከት ያላቸው የውስጥም ሆነ የውጭ በተለይ ደግሞ በአሜሪካ የሚገኙት ሒይውማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ኦክላንድ ኢንስቲትዩትና እንዲሁም ሰርቫይቫል ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል የተባለ በኬንያ የሚገኝ ተቋም የመንደር ማሰባሰቡን ተግባር ክፉኛ እየተቃወሙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አንዳንዴ እጅግ ማሾፍ የሚመስል ምክንያት እንደሚሰጡ፣ ከእነዚህም መካከል የቱሪስት መዳረሻነት እያሳጣችሁ ነው የሚል እንደሆነ፣ በአብዛኛው ግን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ነው በማለት ፕሮግራሙ እንዳይሳካ ያልተቋረጠ ጥረት እንደሚያደርጉ አስረድተዋል፡፡

ይህንን እንቅስቃሴያቸውን መመከት የሚቻለው በመንደር የሚሰባሰቡ ዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ነው የሚሉት ሚኒስትሩ፣ በሌላ በኩል በተለያዩ የሕዝብ ግንኙነት አውታሮች ተከታታይ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...