Sunday, April 21, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጤናማ ያልሆነ የግብር አሰባሰብ እንዳለ አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ባለፉት አራት ወራት የሰበሰበው ግብር ከታደው በታች እንደሆነ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞገሥ ባልቻ ገለጹ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች የባለሥልጣኑን የሥራ አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በበጀት ዓመቱ ያለፉት አራት ወራት ውስጥ በተለይ የግብር ከፋዮችን የሕግ ተገዢነት ማረጋገጥ ላይ ከፍተኛ ክፍተት እንደታየና ከአዲስ አበባ ብቻ 81 ግብር ከፋዮች ላይ ርምጃ መወሰዱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ ዕርምጃ ከተወሰደባቸው 81 ግብር ከፋዮች ውስጥ አብዛኞቹ ከመርካቶ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በ2010 በጀት ዓመት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 199.11 ቢሊዮን ብር እንዲሰበስብ የጸደቀለትን መጠን ወደ 230 ቢሊዮን ብር አሳድጎ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ያወጣ ቢሆንም የአራት ወራቱ አፈጻጸም ግን የዕቅዱ ስኬት ላይ ጥያቄን አጭሯል፡፡

የ2010 በጀት ዓመት የፌዴራል በጀት 320.8 ቢሊዮን ብር ሆኖ እንደጸደቀ የሚታወስ ነው፡፡

በሩብ  የበጀት ዓመቱ ወራት 72 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 62 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ ይህ ከዓመታዊ ዕቅዱ ጋር ሲነጻጸር አፈጻጸሙ  27 በመቶ ነው፡፡ የግብር አሰባሰቡ ጤናማ ነው ሊባል የሚችለው አፈጻጻሙ ቢያንስ 33 በመቶ ቢሆን እንደነበረም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች