Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትወፎች ስንት ዕንቁላል ይጥላሉ?

ወፎች ስንት ዕንቁላል ይጥላሉ?

ቀን:

በአማካይ ብዙዎቹ ወፎች በተወሰነ ጊዜ በቂ ቁጥር ያለው ዕንቁላል ይጥላሉ፡፡ ለምሳሌ ከጎጇቸው የተለቀመ ዕንቁላል እንደሚያመለክተው ግሮስ (Grouse)  36፣ የእንግሊዝ ስፓሮው (English Sparrow)  51፣ ፍሊከር (Flicker) 71፣ የማላርድ ዳክዬ  (Mallard Duck) 146 እና ፎውል (Fowl) 309 ዕንቁላል ጭር ከማለታቸው በፊት ይጥላሉ፡፡ ትልቁ ቁጥር የተመዘገበው የቤት ዶሮ በ365 ቀን 363 ዕንቁላል ስለመጣሏ ሲሆን፣ በዚህም ዶሮዋ በቀን አንድ ዕንቁላል እየጣለች እንደሆነ ይገመታል፡፡

ዕንቁላላቸውን በራሳቸው የማይፈለፍሉ

ብዙዎቹ ወፎች ዕንቁላላቸው ላይ በመቀመጥ ይፈለፍላሉ፡፡ አንዳንድ ዝርያዎች ግን ራሳቸውን ከእንዲህ ዓይነቱ ድግግሞሽ (አሰልቺ ሥራ) ነፃ ወጥተዋል፡፡ ለምሳሌ የማውንድ ወፎች (Mound Birds/Brush Turkeys) የሚባሉት በአውስትራሊያ፣ ምሥራቅ ኢንዲስና አካባቢው የሚገኙ ሲሆን፣ ዕንቁላላቸውን የሚጥሉት በእንጨት ስብርባሪ፣ በቅጠልና ቆሻሻ ነገሮች በሠሩት ክምር ላይ ነው፡፡ ክምሩ ላይ ካስቀመጡት በኋላ ግን ዕንቁላሉን ይሸፍኑታል፡፡ ከዚያም ከፀሐይ የሚወጣው ሙቀትና ቅጠላ ቅጠሎቹ ሲበሰብሱ የሚፈጠረው ሙቀት ዕንቁላሎቹን እንዲፈለፈሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህም የቡድናቸው ማስፈልፈያ ማሽን ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንዱ ክምር ቁመቱ አራት ሜትር፣ ዙሪያው ከ9 እስከ 11 ይደርሳል፡፡ በአፍሪካ የሚገኘው የአዞ ወፍም (Crocodile Bird) ዕንቁላሉን አሸዋ ውስጥ በመቅበር ከፀሐይ በሚገኘው ሙቀት እንዲፈለፈሉ በማድረግ ተመሳሳይ ተግባር ይፈጽማል፡፡

የጓዳ ሥራ የሚተገብሩ ወንዶች

የብዙዎቹ ዓይነት የወፍ ዝርያዎች ወንዶች ዕንቁላል በመፈልፈል ይታወቃሉ፡፡  ነገር ግን በጣም ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት ፍላሮፕ (Phalarope) የሚባሉት በአሜሪካ የሚገኙ የወፍ ዝርያዎች ናቸው፡፡ ፍላሮፕ ለሚስታቸው ታዛዥ የሆኑ ባሎች ናቸው፡፡ ለየት ከሚያደርጓቸው ነገር መካከል ሴቶቹ ከወንዶቹ ይልቅ ደማቅ ቀለም ያላቸውና በመጠን ትልቅ መሆናቸው ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ባብዛኛው የወፍ ዝርያ ላይ የሚታይ አይደለም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ወንዶቹ ደማቅ ቀለም ሲኖራቸው፣ የማሽኮርመሙን ተግባር የሚወጡትም እነሱ ናቸው፡፡ የፍላሮፕ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ወንዱ ጎጆ ይሠራል፤ ሴቷ ታሽኮረምመዋለች፡፡ ዕንቁላሉ ከተጣለም በኋላ አጠቃላይ የማስፈልፈሉን ተግባር ወንዱ ይረከባል፡፡

በወንዶቹ ወፎች የሚደረገው ዕርዳታ ሙሉ ለሙሉ ከራስ ወዳድነት የፀዳ አይደለም፡፡ በፍልፈላ ወቅት አንዳንድ ወፎች ደረታቸው ላይ የሚያቃጥል ክፍል ይኖራቸዋል፡፡ ቀዝቃዛውን የዕንቁላል ሽፋን መታቀፋቸው ግን ማቃጠሉን ረገብ ያደርግላቸዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ይኼ ግምት ውስጥ ሲገባ ታዲያ የወንዶቹ ተግባር ለራስም ጥቅም ነው ያስብል ይሆናል፡፡

  • ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...