Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ​​​​​​​አይኤስ በሚል ምሕፃር የሚታወቀው አሸባሪ ድርጅት ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ...

​​​​​​​አይኤስ በሚል ምሕፃር የሚታወቀው አሸባሪ ድርጅት ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝ ባለፈው ረቡዕ (ሚያዝያ 14) በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ቁጣውን ለመግለጽ ትዕይንተ ሕዝብ ያደረገው ከተሜ ከ30 ሰማዕታቱ መካከል የሁለቱን ፎቶግራፍ ይዞ

ቀን:

እግዜር ፖለቲካው

እግዜር ፖለቲካው ዝም! – ዝም እግዜር ፖለቲካው
እንጃ ሌላውን፣ እኔን ግን ሲገርመው

ይሄ ዝምታው

እንዲህ ያለ ዝምታ ምንድነው?

* * *

ዝም ማለትእንዲህ ዝም

መደበት

ዐላይነቱ ዐይነት፡
አለው ከሚባለው አንጀቱ አንፃር
አባትነት
እማይረዱትእማይረዱት ምስጢር፡፡

* * *

እንዴት ጭጭእንዲህ ዝም ብሎ ማየት!?
ዘመናዊ ነፍጠኛ ሲጫወት
ሰው አጋድሞ ይባርክ ብሎ ሲያወራርድ
ሲያርድ

ቆዳውን ገፍፎ ሲገደግድ
ግድግድ ነቅሎ በፖለቲካ ገበያ ሲነግድ!?

* * *

አብሮም፣ ያጠባ ጡትን ሲጎምድ
ሙዳ ሥጋ ይመስል
ከወለደ ማህፀን ስለት ሲሰድ
ስምጥ!!
ነገሩን ያየ ቀርቶ የሰማን የሚሰቀጥጥ፣
እንዴት ይቻላል ዝም ማለት ዝም
አለመታመም
ላጤነው የእግዜሩ ፖለቲካ ሲገርም፡፡

  • ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው ‹‹የተጉዋጎጠ ልብ››

እነሆ እንጉርጉሮ!

በዚህ የሽምግልና ዕድሜዬ (79) በጣም ከሚያሳዝነኝ  ነገር አንዱ፣ በስደተኞች ወገኖቻችን በተለይም በአንዳንድ የአፍሪካና የዓረብ አገሮች በሚሰደዱት ላይ በየጊዜው የሚደርስባቸው ፍዳና መከራ ሲሆን፤ የዚህ ሰሞኑ  ደግሞ መረን የለቀቀ እጅግ አሰቃቂ ነው! በደቡብ አፍሪካ የተፈፀመውማ ማንዴላን የመሰለ ታላቅ ሰውና ኤኤንሲ የመሰለ ስመ ጥር ታጋይ ድርጅት ካፈራ አገር የሚጠበቅ ባለመሆኑ መሪር ሐዘን ሁላችንም እንደተሰማን አምናለሁ! ‹‹እንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› እንዲሉ የሊቢያው ‹‹ጭዳ›› ተጨመረበት ! በአባቶቻችን መልካም ዘይቤ ‹‹እግዚኦ! አበስኩ  ገበርኩ፤  ሰውረነ ከመአቱ›› ነው የሚያሰኘው ሰሞኑን በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው ግፍ! በዚህ አጋጣሚ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች ‹‹እግዜር ያጥናችሁ! ብርታቱን ይስጣችሁ!›› እላለሁ በትህትና። የ‹‹እዝንም›› እነሆ እንጉርጉሮ !

“የሰው አውሬ!

     

አውሬነቱን ያልጨረሰ

‹‹ጭራቅ›› የባሰ!

እንደ በግ ፍሪዳ

ሰው አርዶ የሚበላ 

የሰው ደም የተጠማ

እርኩስ ወራዳ  

ለካ ‹‹የሰው አውሬ›› አለና

በደቡብ አፍሪካ!

ይህን ጉድ ሳያይ

ይህን ስቃይ

እንኳን ሞተ! ተቀበረ!

ማንዴላኮ ሰው ነበረ! ! !

******

መታሰቢያነቱ በደቡብ አፍሪካ ለተሰዉ ወገኖቻችን

አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ ከላስ ቬጋስ አሜሪካ (ሚያዝያ 12፣ 2007)

***********

ትዕቢትና ቁጣ

ከልብህ የሚሰርፀው ቁጣህን ተቆጣጠረው፡፡ ቁጣ ጥበብን ያጠፋልና፡፡ ሰዎች በዚህ ዓለም አብረው ይኖሩና ይዋደዱም ዘንድ እርስ በርሳቸውም ይረዳዱ ዘንድ ካዘዘ ከፈጣሪ ፈቃድ ጋርም አይስማማም፡፡ ቁጡዎች በሰላም አብረው መኖርን አይችሉም፡፡ ሁልጊዜ እርስ በርሳቸው ይጣላሉ፣ ይሰዳደባሉ፣ ይደባደባሉ፣ ይገዳደላሉ እንጂ፡፡ አንተ ግን እንደነርሱ አትሁን፡፡ በጥበብና በስውር መንገድ ኑሮህን አሳምረው እንጂ፡፡ በትግልና በመበራታትም አይደለም፤ የሕይወት ጣዕም በተሰወረና ትሁት በሆነ አኗኗር ይገኛልና፡፡ ስለዚህም ከትዕቢት ሁሉ ራቅ፣ ልብህም አይታበይ፣ ከታላላቆች ጋርም አትሂድ፣ ከክቡራን ጋርም አትተባበር፡፡

በሌሎች ላይም ትከብር ዘንድ አትሻ፡፡ በሕዝብ መካከል እኩልና ስውር ሁነህ ኑር እንጂ፡፡ ለራስህም ብዙ ሰላም ታገኝበታለህ፡፡ ወደታች ወይም ወደሜዳ የሚመላለስ መውደቅን አይፈራምና፡፡ ከግንብ ላይ የሚወጣ ግን መውደቅን ይፈራል፡፡ ወደላይ ከፍ ያለውን ያህል ወደ ታች ቢወድቅ ስብራቱ የጸና ይሆናልና፡፡ እንዲሁም በሕዝብ መካከል ተሰውሮ የሚኖር መከራ አያገኘውም፡፡ በሕዝብ ዘንድ ተከብሮ ከፍ ከፍ ያለ ግን ይወረዳል፣ መከራም ያገኘዋል፣ በሰዎች ሁሉ ዘንድ ቅንዓትና ጸብ ይጸናበታል፡፡

አለቃ ያሬድ ፈንታ ወልደ ዮሐንስ ‹‹ሐተታ ዘርዐ ያዕቆብ ወሐተታ ወልደ ሕይወት›› (2007)

************

ወዮ

ወዮ ለኔ ስደት

ስንቱን እየሰማሁ

ሰምቼ እየረሳሁ

‹‹ሙጥኝ›› ብዬው ኖሬ

ስንቱን አይቼበት

ስንቱን አጥቼበት

ለውጬው ባገሬ

ዛሬ ካራ ስሎ ከፊቴ ቢመጣ!

እንዲህ ልተራመስ የምሆነው ልጣ?

ወዮ ለኔ ስደት

የሆነ ሰዐት ላይ አብጬ አብጬ ልፈነዳ ደረስኩ

ሃዘኔ፣ ፍርሃቴ፣ ጭንቀቴ፣ ጉጉቴ

ልመለስ? ልሰንብት? ክርክር ሙግቴ

ሞልተው ጠቅጥቀውኝ አንዳች ነገር አከልኩ

ሰማዩን ጎተትኩት መሬት ላይ ወደቀ

የቆምኩበት ምድር ከብጄው ደቀቀ

ወይኔ!

የት ነበርኩኝ ያኔ?

ወዮ ለኔ ስደት

ደሞ ቆየሁና

ካገራቸው መሃል ለብቻዬ ቆሜ

በትንፋሻቸው ኃይል መንሳፈፍ ደክሜ

አየሁት እራሴን ከገለባ ቀሎ

ሥጋ አጥንቱ ክዶት ባየሩ ላይ ዋሎ

አየሁት እራሴን

እፍፍእያሉ ገፍተው

ከውኃ ዳር ወስደው እስከሚያደርጉት

ሲገፉት ሲገፋ

ሲረግጡት ሲዳፋ

አየሁት እራሴን ገለባው ገላዬን በመገፋት ደቆ

የደቀቀው እኔ ከጉልበታቸው ስር ተበታትኖ ወድቆ

አየሁ ካለሁበት

ወዮ ለኔ ስደትTop of Form

Bottom of Form

 

  • ብሩክታዊት ጎሳዬ

ወገን ለወገኑ

ወገን ለወገኑካልተቆረቆረ፣

ጭንጋፍ ፅንስነው እንጂ

ተወልዶያልኖረ።

ዋይ ዋይ ዋይ ____

እሪ በል ያገር ሰው፣

ባንድነት ማልቀስ ነው፣

ከልብ የሚያደርሰው፣

እግዚኦ እግዚኦ እግዚኦ

እንበል ስማኝ ያገሬ ሰው፣

ባንድ ልብ ሲሆን ነው፣

ፀሎት የሚሰምረው፣

ወገን ለወገኑ ካልተቆረቆረ፣

ጭንግፍ ፅንስ ነው እንጂ

ተወልዶም አልኖረ

– ሰርክዓለም አልታዬ

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...