Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አሠልጣኝ ቀጠረ

ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አሠልጣኝ ቀጠረ

ቀን:

ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከኢትዮጵያ ክለቦች በርካታ የውጪ አሠልጣኞችንና ባለሙያዎችን በማስመጣት እያሠራ ይገኛል፡፡ ተጨዋቾችንም በማስመጣትና በክለቡ ስም በማሰለፍ ብዙ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ የአፈጻጸም ሒደቱ በቀጣይ የሚታይ መሆኑ እንደተጠበቀ በቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) ለሚገኘው የስፖርት ክለቡ አካዴሚ ዳይሬክተር ከውጪ አስመጥቶ በመቅጠርም ፈር ቀዳጅነቱን ተያይዞታል፡፡
ክለቡ ይህንን ሁሉ የሚያደርገው ከኢትዮጵያ ክለቦች ቁንጮነቱ ባለፈ በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች ውጤታማ ክለብ ለመሆን በማሰብ ነው፡፡ ከዚህ ምኞቱ በመነሳት ለዓመታት የውጪ አሠልጣኞችን ቀያይሯል፡፡ በርካታ አፍሪካዊ ተጨዋቾችን አሰልፏል፤ ሆኖም እንደምኞቱ በአፍሪካ መድረኮች ከዙርና ከማጣሪያ ማለፍ ሳይችል ቆይቷል፡፡ አሁንም በቅርቡ ከክለቡ ዋና አሠልጣኝነት በተሰናበቱት ብራዚላዊው ደ ሳንቶስ ምትክ ምንም እንኳ መደበኛ የአሠልጣኝነት ሥራቸውን ሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በኋላ የሚጀምሩ መሆኑን ክለቡ በላከው መግለጫ ቢያሳውቅም፣ ሆላንዳዊ አዲስ አሠልጣኝ ባለፈው ሐሙስ ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዋና አሠልጣኝ እንደሚሆኑ ክለቡ በይፋ አረጋግጧል፡፡
በክለቡ ከተጨዋችነት እስከ ዋና አሠልጣኝነት የደረሰው ፋሲል ተካልኝ ቀጣይ ዕጣ ፈንታን በተመለከተ በክለቡና በፋሲል ተካልኝ መካከል በሚደርሰው ስምምነት መሠረት የሚወሰን እንደሆነም ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ እስካሁን ባለው ግን ቡድኑን በዋና አሠልጣኝነት እየመራ የተጀመረውን የውድድር ዓመት ሙሉ ኃላፊነቱን ወስዶ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡ ፋሲል ቦታውን ለአዲሱ አሠልጣኝ የሚያስረክበው ደግሞ ክለቡ ለ2008 የውድድር ዓመት ቅድመ ዝግጅት በሚጀመርበት ሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ እንደሚሆንም መግለጫው ያስረዳል፡፡
አሠልጣኝ ፋሲል ክለቡን በዋና አሠልጣኝነት ይዞ የሚያሳየው ብቃትን አስመልክቶ መግለጫው ያለው ነገር የለም፡፡ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ያለውን የአሠልጣኞችና ተጨዋቾችን በሚመለከት ስማቸውን መጥቀስ የማይፈልጉ ደጋፊዎች፣ ‹‹ክለቡ ለውጪ ተጨዋቾች ግዥና ለአሠልጣኞች ቅጥር በአጠቃላይ ተያያዥ ለሆኑ ባለሙያዎችና ሌሎችም በውጪ ምንዛሪ የሚያወጣው ወጪ ጥቂት የማይባል ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ክለቡ የራሱን ስታዲየም፣ የልምምድ ሜዳና ተያያዥ ማዘውተሪያዎች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፤›› በማለት የክለቡን አካሄድ ይተቻሉ፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን እግር ኳስ ክለብ በቀጣይ ዓመት ለሚጠበቀው አህጉራዊና የውስጥ ውድድሮች ለማሠልጠን በይፋ ፊርማቸውን ያኖሩት ሆላንዳዊው ማርቲን ኩፕማን የሁለት ዓመት ኮንትራት እንደተሰጣቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡ በሆላንድ ጉልደርስ እ.ኤ.አ. 1956 ዓ.ም. እንደተወለዱ የሚነገርላቸው ማርቲን ኩፕማን የተጨዋችነት ዘመናቸውን በጎ ኤሄድ ኤግልስ፣ ኤፍሲ ቲዎንቲና ኤሲ ካምበር በተሰኙ ክለቦች የተጫወቱ ከመሆናቸው ባሻገር በአሠልጣኝነት ተዘዋውረው የሠሩባቸው አገሮች በአፍሪካ የኮንጎውን ኤኤል ቪታ ክለብና ሌሎችም ማሠልጠናቸው ተገልጿል፡፡ ሆኖም አሠልጣኙ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በሚኖራቸው ቆይታ ስለሚከፈላቸው የፊርማና ወርኃዊ ክፍያ መግለጫው ምንም ያለው ነገር የለም፡፡
በሌላ በኩል ቅዱስ ጊዮርጊስ በቢሾፍቱ ላይ ላስገነባው አካዴሚ ሆላንዳዊው ሬኒ ሔድኒክን በዳይሬክተርነት መቅጠሩ ይታወሳል፡፡ ሬኒ ሔድኒክ ሆላንዳዊ እንደመሆናቸው ለዋናው ቡድን አዲሱ አሠልጣኝ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ምክንያት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ የሚናገሩ አሉ፡፡ በተያያዘም ቅዱስ ጊዮርጊስ በአገሪቱ ያለውን የበረኞች አሠልጣኝ ክፍተት ለመድፈን የውጪ የበረኞች አሠልጣኝ ቅጥርም እያከናወነ መሆኑ ታውቋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...