Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  አትሌት ኃይሌን የምርቶቹ አምባሳደር ያደረገው ዜድቲኢ የስማርት ስልኮች ፋብሪካ እገነባለሁ አለ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ባለፉት አሥራ አምስት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌኮም ኔትወርክ ዝርጋታ ሥራዎች ላይ ሲሳተፍ የቆየው ዜድቲኢ ኩባንያ በአገር ውስጥ የሚገጣጠሙ የስማርት ስልኮች ፋብሪካ የመገንባት ፍላጎት እንዳለው ይፋ አደረገ፡፡

  ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በተካሔደ ሥነ ሥርዓት የዜድቲኢ ከፍተኛ ኃላፊዎችና የሕዳሴ ሞባይል ኩባንያ አመራሮች እንዲሁም አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ስምምነት ፈጽመዋል፡፡ የሕዳሴ ሞባይል አመራሮች በአገሪቱ የሚገነባውን የስማርት ስልኮች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከዜድቲኢ ጋር ዕውን ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡ ይገነባል ተብሎ የሚጠበቀው ፋብሪካ 4G ኔትወርክ ተርሚናሎችን ጭምር የሚቀበሉ ምርቶች የሚገጣጠሙበት እንደሚሆን የኤድቲኢ የአፍሪካ ተርሚናል ቢዝነስ ምክትል ፕሬዚዳንት ዲንግ ሃዎ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ፋብሪካውን ለመገንባት ጥናት እየተካሔደ ይገኛል፡፡ ዜድቲኢ ከሚገነባው ፋብሪካ ባሻገር፣ በአገር ውስጥ ለዝቅተኛውና ለመካከለኛው ተጠቃሚ ሲያቀርባቸው ከነበሩት የሞባይል ስልኮች በተጨማሪ አዳዲስና ለከፍተኛ ተጠቃሚዎች የሚውሉ ስማርት ስልኮችን ይፋ አድርጓል፡፡

  በአብዛኛው ከ3G የሞባይል ኔትወርክ ጋር ተጣምረው የሚሠሩ ተርሚናል ምርቶቹን ለገበያ ያቀረበው ዜድቲኢ፣ በድምጽ አማካይነት አገልግሎት የሚሰጡ የረቀቁ ስልኮችንም ለገበያ አቅርቧል፡፡ በቅርቡም 4G ኔትወርክን የሚቀበሉ ስልኮች ገበያው ውስጥ እንደሚያስገባ ተጠቅሷል፡፡ ብሌድ ኤስ6 የተባለውን ስማርት ስልክ ለታዳሚያኑ ያስተዋወቀው ዜድቲኢ፣ 4G Ufi 4G CPE እንዲሁም 4G USB የተባሉት ስማርት ስልኮችና የኢንተርኔት መገልገያ መሣሪያዎች ወደ ገበያው እንደሚገቡ አስታውቋል፡፡ ዜድቲኢ 4G ኔትወርክ አቅራቢ ከሆኑ ኩባንያዎች በዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ይገልጻል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በ3G ኔትወርክ ዝርጋታ ጋር ከሌላው የቻይና ተቀናቃኙ ሁዋዌ ጋር ተጋርቶ እየተሳተፈ ሲሆን፣ ሁዋዌ አዲስ አበባ ላይ የ4G ኔትወርክ ዝርግታን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ሁለቱ ኩባንያዎች በጠቅላላው የ1.6 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክቶች እኩል ተካፍለው እየሠሩ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ግን ዜድቲኢ ብቻውን የ1.5 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በመውሰድ የአገሪቱን የሞባይል ኔትወርክ መዘርጋቱ አይዘነጋም፡፡

  በሌላ በኩል አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ የዜድቲኢ ምርቶች የብራንድ አምባሳደር በመሆን ለመሥራት ስምምነት አድርጓል፡፡ አትሌት ኃይሌ ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ከዜድቲኢ ጋር ለመሥራት የተስማማበት የገንዘብ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ የዜድቲኢ አመራሮች የኩባንያ ምሥጢር እንደሆነ በመግለጽ ይፋ ከማድረግ ተቆጥበዋል፡፡

  ህዳሴ ሞባይል፣ ከኢትዮቴሌኮም በተቀነሱ 2,508 ሠራተኞች የተቋቋመ የአክሲዮን ኩባንያ ሲሆን፣ በአገሪቱ የቴሌኮም ገበያ ውስጥ ድርሻ ከመያዝ ባሻገር በተለያዩ የሞባይል ተጨማሪ እሴት አገልግሎቶች ላይ ለመሳተፍ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በ75 ሚሊዮን ብር ገደማ የተቋቋመው ህዳሴ ሞባይል፣ ባለፈው ዓመት 29.9 ሚሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ ማግኘቱንም አስታውቋል፡፡

   

  spot_img
  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች