Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓለም መንግሥታት በአሸባሪዎች ላይ እንዲረባረቡ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓለም መንግሥታት በአሸባሪዎች ላይ እንዲረባረቡ ጥሪ አቀረበ

ቀን:

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ተማሪዎችና ሠራተኞች የ30 ኢትዮጵያውያንን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ የቀጠፈውን አሸባሪ ቡድን አይኤስ አወገዙ፡፡ በሰሜን አፍሪካዊቷ ሊቢያ አረመኔያዊ ግድያ ለተፈጸመባቸው ወገኖች የተሰማቸውን መሪር ሐዘን ገልጸው፣ የዓለም መንግሥታት ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙና አሸባሪዎቹ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሚያዝያ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ ሕንፃ አዳራሽ ውስጥ በተዘጋጀው የሐዘን መግለጫ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ፣ ‹‹አሸባሪውና ነፍሰ ገዳዩ ቡድን አይኤስ በሊቢያ በረሃ ውድ ወገኖቻችን ላይ የፈጸመው እጅግ ዘግናኝና ፍፁም አረመኔያዊ ድርጊት በእኛ በኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የሰው ልጅ ላይ የተቃጣ የጥፋት ድርጊት ስለሆነ የዓለም ሰላም ወዳድ ሕዝቦች በመሉ እነዚህን በማናለብኝነት የሚንቀሳቀሱ አረመኔ ወንጀለኞች ከምድራችን ለማስወገድ በአንድነት ሊነሱ ይገባል፤›› ሲሉ የተቋሙን አቋም ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ወንጀለኞቹ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ በመሪር ሐዘንና በሰቆቃ የተሞላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እንደሚሻ ተናግረዋል፡፡ በሐዘን መግለጫው ወቅት በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ በግፍ የደረሰው ጥቃትም ተወግዟል፡፡ ዶ/ር አድማሱ፣ ‹‹በደቡብ አፍሪካ ጎጠኞች በወገኖቻችን ላይ የፈጸሙት አረመኔያዊ ግድያና ዝርፊያ ኢ-ሰብዓዊና ወደር የማይገኝለት የክፍለ ዘመናችን አስከፊ ወንጀል በመሆኑ አጥብቀን እንቃወማለን፤›› ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በሥነ ሥርዓቱ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ መምህራንና ተማሪዎች ድርጊቱ ዓለም የደረሰበትን የሥልጣኔ ደረጃ የሚፃረር አሳፋሪ ምግባር ነው ብለዋል፡፡ ዜጎች አገራቸውን ለቀው ከሚሰደዱባቸው ምክንያቶች ቀዳሚው የሁኔታዎች አለመቻቸት በመሆኑ፣ መንግሥት ጉዳዩን በአትኩሮት እንዲመለከተው ያሳሰቡ መምህራን ነበሩ፡፡ ተቋሙም ኢ-ሰብዓዊውን ድርጊት ከማውገዝ ባለፈ ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ኃላፊነቱን እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዶ/ር አድማሱ በበኩላቸው፣ ተቋሙ በንፁኃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግፍና በደል አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የሚወስዱትን ዕርምጃ ሙሉ በመሉ እንደሚደግፍም አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያውያኑ ዕልቂት ከተሰማ በኋላ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የተለያዩ አገሮች፣ የመንግሥትና የግል ተቋማት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል፡፡ በአይኤስ ለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች የገንዘብ ዕርዳታ የሰጡ ድርጅቶችም ይጠቀሳሉ፡፡ ከሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት ብሔራዊ ሐዘን መታወጁና በዚያኑ ዕለት በመስቀል አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሃይማኖት መሪዎችና የከተማው ነዋሪዎች በተገኙበት ሰላማዊ ሠልፍ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...