Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየሽብር ወንጀል ለመፈጸም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል የተባሉ ግለሰቦች ተከሰሱ

  የሽብር ወንጀል ለመፈጸም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል የተባሉ ግለሰቦች ተከሰሱ

  ቀን:

  በምሥራቅ ሸዋ ዞን አድአ ወረዳ ቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ በሴል በመደራጀትና በህቡዕ በመንቀሳቀስ የሽብር ተግባር ወንጀል ለመፈጸም ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል የተባሉ አራት ግለሰቦች፣ ዓርብ መጋቢት 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

  ተከሳሾቹ ፈለቀ ገብረ ሕይወት፣ ተገኝ ጀማነህና ክፍሌ ወዳጆ በቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ ሰለሞን ብሩ የተባለው ተከሳሽ ደግሞ በሞጆ ከተማ ነዋሪ መሆኑን ከሳሽ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

  ተከሳሾቹ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ)፣ 38 እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 7(1) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ፣ አሜሪካ ከሚኖሩት የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ተፈሪ ካሳና መስፍን ፀጋዬ የሚሰጣቸው የገንዘብ ድጋፍና የዓላማ ተልዕኮ ለመፈጸም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ እንደነበር ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገለጿል፡፡

  ተከሳሾቹ አባላትን በህቡዕ በመመለመል በተለያዩ አገሮች ካሉ የቡድኑ አባላት በሚላክላቸው ገንዘብ የጦር መሣሪያ ገዝተው በማስታጠቅ፣ ከኡጋንዳ በሞያሌ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላትን ወደ አርባ ምንጭ ለመውሰድ ሐሰተኛ መታወቂያ በማውጣት እንዲጓጓዙ ማድረጋቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ ዋርዬ ጃተኒ ከተባለ የሞያሌ ከተማ ቀበሌ 02 ሊቀመንበር ለአንድ መታወቂያ 100 ብር በመክፈልና ትራንስፖርት ከፍለው ወደ አርባ ምንጭ በመላክ፣ አርባ ምንጭ መቀመጫውን ካደረገ የሽብር ቡድን አባላት ጋር እንደተገናኙም ተጠቁሟል፡፡

  በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) ከተማ አባላትን በህቡዕ በመመልመል፣ በሴል በማደራጀት፣ የገንዘብ ድጋፍ በውጭ ካሉ የድርጅቱ አመራሮች በማግኘት የሽብር ተግባር ወንጀል ለመፈጸም መሣሪያ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ሥር በመዋላቸው፣ በሽብር ቡድን ውስጥ በመሳተፍ ወንጀል ክስ እንደመሠረተባቸው ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ገልጿል፡፡

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ‹‹መንግሥት የሕዝብን ደኅንነት ባለመጠበቁ  መንግሥት ነኝ የማለት ልዕልና የለውም›› የፖለቲካ ፓርቲዎች

  የወለጋ ዞኖች በኮማንድ ፖስት ሥር እንዲተዳደሩ ተጠየቀ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ...

  ጎህ ቤቶች ባንክ ወደ ቤት ልማት ለመግባት ብሔራዊ ባንክን ፈቃድ ጠየቀ

  በስምንት ወራት ውስጥ 7.9 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስታውቋል ኢትዮጵያ ውስጥ...

  የመንግሥት ተቀዳሚ ኃላፊነት ንፁኃንን ከአጥቂዎች መከላከል ነው!

  በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ንፁኃን ያለ ኃጢያታቸው የሚጨፈጨፉበት ምክንያት ብዙዎችን...

  የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት አካታችነት ሁለት በመቶ ብቻ መሆኑ ተገለጸ

  በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች በሥራ ሥምሪት መካተት እንዳለባቸው የሚገልጽ አዋጅ...