Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹ኢትዮጵያ በእኔ ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት››

‹‹ኢትዮጵያ በእኔ ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት››

ቀን:

የጂቡቲ ፕሬዚዳንት

በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የተገኙት የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ሐሙስ መጋቢት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ  በፓርላማ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ግላዊ ስሜት፣ በጂቡቲና በኢትዮጵያ መካከል ኢኮኖሚያዊ ውህደትን መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

 ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ የመጡት ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲሆን፣ የተለያዩ የትብብር ስምምነቶችን ፈርመዋል፡፡

‹‹ሁላችሁም እንደምታውቁት ኢትዮጵያ በእኔ ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት፡፡ ምክንያቱም አባቴ በኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ጣቢያ በሚሠራበት ዘመን የተወሰኑ ዓመታት በልጅነት ያሳለፍኩት እዚህች ታላቅ አገር ውስጥ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የሁለቱ አገሮች የወደፊት ዕጣ በታሪክ፣ በደም፣ በኢኮኖሚና በሌሎች ብዙ መንገዶች መተሳሰራቸውንም ገልጸዋል፡፡ ሁለቱ አገሮች ዘመናዊ የባቡር መስመር በመገንባት ትብብርና ወዳጅነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያደርጉት እንቅስቃሴም፣ ለምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ምሳሌ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

‹‹የዚህች ቅኝ ያልተገዛች አገር ታሪክ ለአፍሪካውያን ኩራት ነው፤›› ያሉት የጂቡቲው ፕሬዚዳንት፣ በቀጣይ ቀናት ቆይታቸው የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡ ከእነዚህ ስምምነቶች መካከል በፍትሕና ሕግ ነክ ሥልጠና፣ በጋራ የሕግ ድጋፍ እንዲሁም በንግድ ዘርፎች፣ ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠትና ለመተባበር በሁለቱ መንግሥታት መካከል ስምምነት ተደርጓል፡፡

ኢትዮጵያና ጂቡቲ በኢኮኖሚው ዘርፍ የጀመሩት ትብብር ወደ ውህደት እያመራ እንደመሆኑ ሁሉ በፖለቲካና ማኅበራዊ ዘርፎች፣ እንዲሁም በደኅንነትና በባህላዊ ጉዳዮች የተጠናከረ ትብብር እንዲመሠርቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጠይቀዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...