Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየቅዱስ ጊዮርጊስ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ጉዞ

የቅዱስ ጊዮርጊስ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ጉዞ

ቀን:

በአገር ውስጥ የእግር ኳስ ውድድሮች ስኬታማ መሆን የቻለው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ፣ በአፍሪካ መድረኮች የመሳተፍ ዕድል ቢያገኝም በውድድሮቹ ላይ ከመሳተፍ ባሻገር እምብዛም የሚጠቀስ ስኬታማ ጉዞ ሲያደርግ አልተስተዋለም፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን 13 ጊዜ ማንሳት ችሏል፡፡ በአገር ውስጥ ያለውን ውጤታማነት በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ለማሳደግ በተለያዩ የውድድር ዘመኖች፣ የውጭ አገር አሠልጣኞችን በመቅጠር ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዘንድሮ የቶታል ካፍ አፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ተሳታፊ መሆን የቻለው ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ከቀድሞ በተሻለ መልኩ የመጀመሪያዎቹ 16 አገሮች ምድብ ውስጥ ለመቀላቀል እሑድ መጋቢት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በ2017 የካፍ ሻምፒዮን ሊግ የመጀመሪያ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ ከኮንጎው ከሪፐብሊክ ክለብ ኤስ ሊኦፓርድስ ጋር የተደለደለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጭ ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ በምንተስኖት አዳነ የሃያ አራተኛ ደቂቃ ጎል 1 ለ 0 አሸንፎ የቀጣይ ዕጣ ፋንታውን ማስፋት ችሏል፡፡

እሑድ፣ መጋቢት 3 ቀን 2009 ዓ.ም.  የመጀመሪያ ጨዋታውን ያከናወነው ክለቡ፣ የመጨረሻዎቹ 16 ውስጥ ለመቀላቀል ኤስ ሊኦፓርድስን ያስተናግዳል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሲቬልሱ ኮት ዲኦር ጋር ያከናወነውን ጨዋታ 5 ለ0 በሆነ ድምር ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ይህን የደርሶ መልስ ጨዋታ በድምር ውጤት አሸንፎ የምድብ ውጤቱን አስጠብቆ መውጣት ከቻለ፣ የ500 ሺሕ ዶላር ወይም 11.5 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ይሆናል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ ክለቡን በውጪ አገር ተጫዋቾች እያጠናከረ የመጣው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘንድሮ ብዙ ርቀት ለመጓዝም ሰፊ ዕድል እንዳለው እየተነገረ ይገኛል፡፡

ለዚህም ማሳያነት የ10 ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ መሆን የቻለው የኮንጎው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ቲፒ ማዜምቤ ውጤት እንደ ቀድሞ አለመሆን ተጠቃሽ ነው፡፡

ባለፈው እሑድ የዚምባብዌውን ሲኤፒኤስ ዩናይትድ ጋር የተገናኘው ቴፒ ማዜምቤ በሜዳው አንድ ለአንድ መውጣቱና ውጤቱን በቀጣይ ጨዋታ መቀየር ካልቻለ ከውድድር የመውጣቱ ዕድል ሰፊ ይሆናል፡፡  

ከአገር ውስጥ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ከመጎናፀፍ ባሻገር በካፍ ዋንጫ ውድድሮች ላይ ብዙ መራመድ ያልቻለው ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን ያለው የተጨዋቾች ጥምረት ለውጤቱ እንደ ስኬት ይጠቀሳል፡፡

ክለቡ ከካፍ የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ባሻገር የ18ኛ ሳምንት ጨዋታን ሲያከናውን በ35 ነጥብ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሠንጠረዥን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡

በዘንድሮ የቶታል ሻምፒዮንስ ሊግ 46 ክለቦች እርስ በርስ የቀድሞ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ግጥሚያ ካደረጉ በኋላ፣ አሸናፊዎች 23 ቡድኖች ቅድመ ማጣሪያውን በቀጥታ እንዲያልፉ ከተደረጉት ዘጠኝ ቡድኖች ጋር በድምሩ 32 ቡድኖች ወደ አንደኛው ዙር አልፈዋል፡፡

አሁን እየተካሄደ ባለው የአንደኛ ዙር የደርሶ መልስ ፉክክር አሸናፊ የሚሆኑት 16 ቡድኖች፣ ጠቀም ያለ ገንዘብና አንድ ክለብ ቢያንስ ስድስት አህጉራዊ ጨዋታዎችን የማድረግ ዕድል ወደሚያገኝበት የምድብ ፉክክር የሚገባ ይሆናል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...