Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየመኸር ሰብል ሽፋን ጥሩ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ገለጹ

  የመኸር ሰብል ሽፋን ጥሩ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ገለጹ

  ቀን:

  በሁለተኛው የዕደገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከ12 ሚሊዮን ሔክታር በላይ የሚሆን ቦታን በመኸር ሰብል ለመሸፈን መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በ8ኛው አገር አቀፍ የአርሶ/አርብቶ አደሮች በዓል በአዳማ በተከበረበት ዕለት ገልጸዋል፡፡

  በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን በመነሻ ዓመት በአገሪቱ የነበረው 191 ሚሊዮን ኩንታል የዋና ዋና ሰብሎች ምርት በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ላይ 270 ሚሊዮን መድረሱንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ረገድም በዕቅድ ዘመኑ መነሻ 3.7 ሚሊዮን ሔክታር የነበረውን ሽፋን ከ8 ሚሊዮን ሔክታር በላይ ማድረስ መቻሉንም አክለዋል፡፡

  ‹‹የወጣቶች ዘመናዊ የግብርና ልማት ተሳትፎ በአግባቡ ከተመራ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ታሪካዊ ተልዕኮውን የሚፈጽም ይሆናል›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና አዳዲስ አሠራሮችን በአነስተኛ አርሶ አደሩ ማሳ ላይ በመተግበር ግብርናና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሠራበት ያለው የፖሊሲ አቅጣጫ ትክክለኛነት የሚያሳይ እንደሆነ በመግለጽ የተመዘገበውን ውጤት አሞካሽተዋል፡፡ በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ከተገኘው 270 ሚሊዮን ኩንታል ምርትም 95 በመቶ የሚሆነው የተገኘው ከአነስተኛ አርሶ አደሩ ማሳ ላይ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

  በአንፃሩ ደግሞ በበጀት ዓመቱ የተገኘው የምርት መጠን ከሌሎች አገሮች ጋር ሲተያይ እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን በመግለጽ ለአገሪቱ በቂ የሚባል ምርት ለማምረት ገና ብዙ መሥራት እንደሚያስፈልግ በበዓሉ ዋዜማ ከአርሶ አደሮች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ ተገልጿል፡፡ ከተሳታፊዎቹ መካከል አንደኛው አስተያየት ሰጪ ‹‹ለምሳሌ ህንድ 900 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ በአንድ ዓመት ውስጥ አምርታለች፡፡ እኛ ጋር ግን የተገኘው አጠቃላይ ምርት 270 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ ነው›› በማለት የተገኘው የምርት መጠን ከዚህ ቀደም ከነበረው አንጻር ጥሩ የሚባል ቢሆንም ከአቅም በታች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

  ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የሞዴል አርሶ አደሮች ሽልማትም ዘንድሮ ለ8ኛ ጊዜ እሁድ የካቲት 2009 ዓ.ም. በአዳማ ተካሂዷል፡፡ ከ550 በላይ ተሸላሚዎችን ያካተተ ሲሆን 60 የሚሆኑት ሴት አርሶ አደሮች ናቸው፡፡ የተሸለሙት አርሶ አደሮች አጠቃላይ የካፒታል መጠናቸው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ፣ እሴት ወደሚጨምሩ የተለያዩ የልማት ኢንቨስትመንትና የንግድ ሥራዎች የተሸጋገሩና ለወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድል የፈጠሩ ናቸው፡፡

  ባፈሩት ካፒታል የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችንና አዳዲስ አሠራሮችን በመጠቀም የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የቻሉና ብዙም የባለሙያ ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው ራሳቸውን ችለው የተሟላ ፓኬጅ የተጠቀሙና ለሌሎችም አርሶ አደሮች ማስተማር የቻሉ ተሸልመዋል፡፡ ከአነስተኛ አርሶ አደርነት ተላቀው የባለሀብትነት ደረጃ ላይ መድረስም ሌላው የሽልማቱ መሥፈርት ነው፡፡ ሜዳሊያና ዋንጫ የተሸለሙ ሲሆን አንደኛ የወጡ 8 አርሶ አደሮች ደግሞ ትራክተር ተሸልመዋል፡፡

  በመድረኩ እንደተገለጸው ይህ አገር አቀፍ የአርሶ አደሮች ሽልማት ለግብርና ምርትና ምርታማነት ከፍተኛ ዕድገት እያበረከተ ይገኛል፡፡ ለአርሶ አደሮቹ ለሥራቸው ውጤት እውቅና እንዲያገኙ መደረጉ በመካከላቸው የሥራ ውድድር እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ መልካም ተሞክሮዎችና የልምድ ልውውጦች እንዲፈሩም እያደረገ ይገኛል፡፡

  እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ይህ የሽልማት ፕሮግራም ከተጀመረ እስካሁን በአገሪቱ ከሚገኙ 14 ሚሊዮን አርሶ አደሮች መካከል 22 በመቶ የሚሆኑትን ሞዴል አርሶ አደር ማድረግ ተችሏል፡፡ በበጀት ዓመቱ የተገኘውን አጠቃላይ ምርት በእጥፍ ለማሳደግ ደግሞ የሞዴል አርሶ አደሮቹን ቁጥር በእጥፍ ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን በመድረኩ የተገኙ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡ 

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...